top of page

እንዳለ  ወልደጊዮርጊስ

Mezmur

  1. የማያቋርጥ ፡ ምሥጋና

  2. ሙላኝ ፡ ተቆጣጠረኝ

  3. የዛሬው

  4. ያው ፡ ነው

  5. ድንቅ ፡ ነህ

  6. ዘላለማዊ

  7. ነፍሴ ፡ ተስፋ

  8. አትደክምም

  9. ምን ፡ አሉ

  10. ክብር ፡ ሁሉ

  11. አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ

  12. ጌታ ፡ ልዩ ፡ ነው

  13. አልፋ ፡ ኦሜጋ

  14. ምህረትህ

እንዳለ  ወልደጊዮርጊስ    1

የማያቋርጥ ፡ ምሥጋና

የማያቋርጥ ፡ ምስጋና ፡ የማያቋርጥ ፡ ዝማሬ 
     ይኸዉ ፡ መጣሁኝ ፡ ጨምሬ [፬X] 

    ምስጋና ፡ ለጌታ [፪X]
    እልልታ ፡ ለጌታ [፪X]

ያጓራ ፡ ጠላት ፡ ያብዛ ፡ ቀረርቶ 
ከሰራዉ ፡ ወጥመድ ፡ ማምለጤን ፡ አይቶ 
ከቶ ፡ አላቆምም ፡ ማመስገን ፡ ማምለክ 
ላዳነኝ ፡ ጌታ ፡ ፊቱ ፡ መንበርከክ 

ሌባዉ ፡ ቀርቶታል ፡ በከንቱ ፡ ዛቻ
ከሩቅ ፡ እያየ ፡ መናደድ ፡ ብቻ [፬X]

    የማያቋርጥ ፡ ምስጋና ፡ የማያቋርጥ ፡ ዝማሬ 
     ይኸዉ ፡ መጣሁኝ ፡ ጨምሬ [፬X] 

    ምስጋና ፡ ለጌታ [፪X]
    እልልታ ፡ ለጌታ [፪X]

ፍጡር ፡ ፈርቼ ፡ የፈጣሪዬን ፡ ምስጋና ፡ አላቋርጥም
ለአሁኑ ፡ ዓለም ፡ ጓግቼ ፡ ዕንቁዬን ፡ ለአፈር ፡ አልሰጥም
በጥቂቱ ፡ ሆነ ፡ በብዙ ፡ የሚያድነዉን ፡ ታምኜ
ልበል ፡ ምስጋና ፡ አምልኮ ፡ የማያቋርጥ ፡ ዝማሬ [፫X]

ታላቁንና ፡ የተፈራዉን
የፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ጌታ ፡ የሆነዉን
አድርጌያለሁኝ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ጌታ
አልደነግጥም ፡ በሌላዉ ፡ ላፍታ 
ለእርሱ ፡ ኖራለዉ ፡ ለእርሱ ፡ ሞታለዉ 
ሥሙ ፡ ጌታዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነዉ [፬X]

    የማያቋርጥ ፡ ምስጋና ፡ የማያቋርጥ ፡ ዝማሬ 
     ይኸዉ ፡ መጣሁኝ ፡ ጨምሬ [፬X] 

    ምስጋና ፡ ለጌታ [፪X]
    እልልታ ፡ ለጌታ [፪X]

እንዳለ  ወልደጊዮርጊስ     2

ሙላኝ ፡ ተቆጣጠረኝ

ጠልቄ ፡ መሄድ ፡ እፈልጋለሁ
የእኔ ፡ እርካታ ፡ የአንተ ፡ ክብር ፡ ነው
ላይ ፡ ላዩን ፡ መሄድ ፡ ይቅርብኝና 
ይስጠም ፡ ሕይወቴ ፡ በህልውና (፪x)

መንፈስ ፡ ቅዱስ (፪x)

አዝ፦ ሙላኝ ፡ ተቆጣጠረኝ
ሌላ ፡ ሕይወት ፡ አይኑረኝ (፬x)

ላንብብ ፡ ቃልህን ፡ ልስማ ሕግህን 
ላድርግ ፡ ስራዬን ፡ ደስ ፡ የሚልህን 
መቅደስነቴ ፡ ለአንተ ፡ ብቻ ፡ ነው
የለኝም ፡ በአንተ ፡ ላይ ፡ ደባል ፡ የማደርገው 
ከምር ፡ ነው ፡ ከልብ ነው
የአንተ መሆን ምፈልገው 
ማንከስ ፡ ይቅር ፡ በሃሳቤ 
ልከተልህ ፡ ቆርጦ ፡ ልቤ

አዝ፦ ሙላኝ ፡ ተቆጣጠረኝ
ሌላ ፡ ሕይወት ፡ አይኑረኝ (፬x)

እኔ ፡ ግን ፡ እኔ ግን (፪x)
በጽድቅህ ፡ ፊትህን ፡ አያለሁ
ክብርህን ፡ ሳይ ፡ እጠግባለሁ (፪x)

ቁርጭምጭሚት ፡ ጋ ፡ ባለው ፡ ሕይወቴ
በቃኝ ፡ አልበል ፡ በዚህ ፡ ረክቼ
ጉልበቴን ፡ እና ፡ ወገቤን ፡ አልፈህ
ተቆጣጠረኝ ፡ ከሁሉ ፡ ልቀህ

በአንተ ፡ ተይዞ ፡ ሁሉ ፡ ነገሬ
ቢያልቅ ፡ ይሻላል ፡ ቀሪ ፡ ዘመኔ

ጠልቄ ፡ መሄድ ፡ እፈልጋለሁ 
የእኔ ፡ እርካታ ፡ የአንተ ፡ ክብር ፡ ነው
ላይ ፡ ላዩን ፡ መሄድ ፡ ይቅርብኝና 
ይስጠም ፡ ሕይወቴ ፡ በህልውናህ (፪x)

መንፈስ ፡ ቅዱስ (፪x)

አዝ፦ ሙላኝ ፡ ተቆጣጠረኝ
ሌላ ፡ ሕይወት ፡ አይኑረኝ (፬x)

እንዳለ  ወልደጊዮርጊስ     3

የዛሬው

አዝ፦ የዛሬው ቀኑ ደስ ይላል 
ልናመሰግን መተናል
ከጠላት እጅ የደናንን
ቸሩ ጌታችን ይመስገን (፫x)
ደጉ ጌታችን ይመስገን (፫x)

ካሉን ያላወቁ ምን ሰባሰሳባቻው 
ዕጣ እንደ ወጣለት ልክ የለው ደስታቻው

በማጉረምረም ዘመን የሚሉት ምስጋና
እንዲህ የሚያስዘምር ምንስ ተገኘና

ካሉ(፪x)

ኧረ ወቶልን ነው የፅድቅ ፀሐይ
የመዳንን መንገድ በኢያሱስ ልናይ (፪x)

አንዳንዶች ነበርን ጠጪ የስካር ሰዎች
ብሎም የአመፅና የአጋንንት እስረኞች
አዎ(2x) 

ልዩ ልዩ ቀንበር ነበር በጫንቃችን 
ከእኛ ላይ ሰበረው ደርሶልን ጌታችን

አዎ አዎ

ከምህረቱ ማዕድ ቆርሶ ሰጠንና 
ኢንዲ ሰበሰበን እንድንል ምስጋና (፪)

ራሱን የሰጠን ያዳነን በመስቀል ለይ ሞቶ
ከዓለም እስክንመጣ ታገሰን ይህቺን ቀን አይቶ
ጌታ ባይደርስልን ይህኔ ነበርን በጨለማ 
ምህረት ላበዛልን አምጡ እንጂ ለክብሩ ምስጋና

አዝ፦ የዛሬው ቀኑ ደስ ይላል 
ልናማሳግን መጥታናል
ከጠላት እጅ የደናንን
ቸሩ ጌታችን ይማስገን (፫x)
ደጉ ጌታችን ይማስገን (፫x)

ካሉን ያላወቁ ምን ሰባሰሳባቻው 
ዕጣ እንደ ወጣለት ልክ የለው ደስታቻው(፪x)

ካሉ(፪x)

በማጉረምረም ዘመን የሚሉት ምስጋና
እንዲህ የሚያስዘምር ምንስ ተገኘና

ካሉ(፪x)

ኧረ ወቶልን ነው የፅድቅ ፀሐይ
የመዳንን መንጋድ በኢያሱስ ልናይ (፪x)

እንዳለ  ወልደጊዮርጊስ     4

ያው ፡ ነው

ዛሬ ፡ ብዬ ፡ የጠራሁት ፡ ቀን ፡ ትላንት ፡ ተብሎ ፡ አልፎ ፡ ሲወራ
ብርቱ ፡ መስሎ ፡ የታየው ፡ ሰው ፡ ለቀብሩ ፡ ሞቱ ፡ ሲሰማ
ፍጥረት ፡ ቦታውን ፡ ለቆ 
የቆመው ፡ ደግሞ ፡ ወድቆ
ቀና ፡ ስል ፡ ኢየሱስ ፡ ያው ፡ ነው
ቀና ፡ ስል ፡ ጌታዬ ፡ ያው ፡ ነው ፡ ነው

ይባላ ፡ ቀና ፡ ይባላ ፡ ቀና
ብርቱ ፡ የሆነ ፡ አምላክ ፡ አለና
ይታይ ፡ ወደ ፡ ላይ ፡ ይታይ ፡ ወደ ፡ ላይ
ዘላለም ፡ ሚኖር ፡ አለ ፡ በሰማይ

አለሁ ፡ አለሁ ፡ ያለው ፡ ሰው
ድንገት ፡ ጉልበት ፡ ሲከዳው
ሁሉን ፡ ዘመን ፡ በቃ ፡ ሲለው
እንደ ፡ ጥላ ፡ ሲያሳልፈው
ንጉሠ ፡ ነገሥት ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ዛሬም ፡ ያው
ግርማዊነቱ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ነገም ፡ ያው

ይባላ ፡ ቀና ፡ ይባላ ፡ ቀና
ብርቱ ፡ የሆነ ፡ አምላክ ፡ አለና
ይታይ ፡ ወደ ፡ ላይ ፡ ይታይ ፡ ወደ ፡ ላይ
ዘላለም ፡ ሚኖር ፡ አለ ፡ በሰማይ

አደራ ፡ የተባለው ፡ ለአደራው ፡ ሳይበቃ
ዓይን ፡ የተጣለበት ፡ ከስፍራው ፡ ሲታጣ
ማነው ፡ ጽኑ ፡ ብዬ ፡ ስጠይቅ ፡ ጥያቄ
ቃሉ ፡ እንዲህ ፡ እያለ ፡ ፈሰሰ ፡ ከውስጤ ፡ 

ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ትላንትናም ፡ ዛሬም ፡ እስከ ፡ ለዘላለም ፡ ያው ፡ ነው

አንቱ ፡ ተብሎ ፡ ሚወራለት
ጐንበስ ፡ ቀና ፡ ሚባልለት
እንዲያው ፡ ሲቀር ፡ በትዝታ
አንደ ፡ እለ ፡ ግን ፡ ሕያው ፡ ጌታ ፡
ንጉሠ ፡ ነገሥት ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ዛሬም ፡ ያው
ግርማዊነቱ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ነገም ፡ ያው

ይባላ ፡ ቀና ፡ ይባላ ፡ ቀና
ብርቱ ፡ የሆነ ፡ አምላክ ፡ አለና
ይታይ ፡ ወደ ፡ ላይ ፡ ይታይ ፡ ወደ ፡ ላይ
ዘላለም ፡ ሚኖር ፡ አለ ፡ በሰማይ

እንዳለ  ወልደጊዮርጊስ     5

ድንቅ ፡ ነህ

ጌታ ፡ ፈጣሪዬ ፡ ስለ ፡ አፈጣጠሬ 
ስለሚያስደንቀው ፡ ስለ ፡ አካል ፡ ክፍሌ

  ላመሰግንህ ፡ እፈልጋለው
  ግሩም ፡ ድንቅ ፡ ሆኜ ፡ ተፈጥሪያለው [፪X]

    ግሩም ፡ ነህ ፡ የሰራሀኝ
    ድንቅ ፡ ነህ ፡ የፈጠርከኝ [፪X]

የማመስገኛ ፡ ምክንያት ፡ ከሆነ
ከቁጥር ፡ በላይ ፡ እኔ ፡ ጋር ፡ አለ
እግሬ ፡ ሲራመድ ፡ ሚዛን ፡ ጠብቆ
ዓይኔም ፡ ሲያይልኝ ፡ ቅርብም ፡ አርቆ
በራስ ፡ ቅሌ ፡ ላይ ፡ ሲበቅል ፡ ፀጉሬ
ጣቶቼ ፡ ላይ ፡ ሲያድግ ፡ ጥፍሬ
ውበት ፡ አላቸው ፡ በየቦታቸው 
ጌታዬ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የሰራሃቸው [፪X] 

    ግሩም ፡ ነህ ፡ የሰራሀኝ
    ድንቅ ፡ ነህ ፡ የፈጠርከኝ [፪X]

ሰው ፡ ሰውን ፡ ቢሰራው 
ቢያበጀው ፡ እስትንፋስ ፡ ቢሰጠው
የሚከፍለው ፡ አጥቶ 
ሁሉም ፡ ሰው ፡ መኖር ፡ በተሳነው

ይተመን ፡ ቢባል ፡ በዋጋ ፡ የአካል ፡ ክፍሌ
በዓለም ፡ ያለው ፡ ሃብት ፡ በሙሉ ፡ አይመጥን ፡ ለኔ
እንዃን ፡ ሁሉንም ፡ ይቅርና ፡ አንዱንስ ፡ እንኳ
መፍጠር ፡ ያልቻለው ፡ የሰው ፡ ልጅ ፡ እንዴት ፡ ይመካ

    ግሩም ፡ ነህ ፡ የሰራሀኝ
    ድንቅ ፡ ነህ ፡ የፈጠርከኝ [፪X]

በሚጥም ፡ ዜማ ፡ የሚያዜመው ፡ የአንተን ፡ ዝማሬ
ገንዘብ ፡ ሊገዛው ፡ አይችል ፡ ይህ ፡ አንደበቴ [፪X]

ጌታ ፡ ፈጣሪዬ ፡ ስለ ፡ አፈጣጠሬ 
ስለሚያስደንቀው ፡ ስለ ፡ አካል ፡ ክፍሌ

 ላመሰግንህ ፡ እፈልጋለው
 ግሩም ፡ ድንቅ ፡ ሆኜ ፡ ተፈጥሪያለው [፪X]

    ግሩም ፡ ነህ ፡ የሰራሀኝ
    ድንቅ ፡ ነህ ፡ የፈጠርከኝ [፪X]

እንዳለ  ወልደጊዮርጊስ     6

ዘላለማዊ

የማታረጀው ፡ ማትቀደደው
ሀሩር ፡ ሲመጣ ፡ ማትቀየረው
ዘላለማዊው ፡ ልብሴ ፡ የኔነቴ: ውበት:ግርማ
ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ ነህ ፡ የክብር ፡ ሁሉ ፡ መደምደሚያ
 
      ዘላለማዊ ፡ ልብሴ ፡ ነህ ፡ ውበቴ [2X]

አንተን ፡ ለብሶ ፡ ተጐናፅፎ 
እራቁቱን ፡ ማንስ ፡ ቀርቶ
የለበሰህ ፡ ከበረ ፡ እንጂ
መቼ ፡ ቆመ ፡ ውርደት ፡ ደጅ
   
  አንተን ፡ ያለ ፡ የታደለ ፡ እራቆቱ ፡ ተሸፈነ [2X] 

    ዘላለማዊ ፡ ልብሴ ፡ ነህ ፡ ውበቴ [2X]

ከአንተ ፡ ውጭ ፡ ሚለበስ ፡ ሁሉ
የማያዛልቅ ፡ ቅጠል ፡ መሆኑ
የተረዳ ፡ ሰው ፡ ሌላውን ፡ አውልቆ
አንተን ፡ ሲለብሰህ ፡ አዳኙን ፡ አውቆ

  የሞትን ፡ ነፋስ ፡ ብርድን ፡ አይፈራ ፡ የዘላለሙን ፡ ለብሶሃልና [2X]

    ዘላለማዊ ፡ ልብሴ ፡ ነህ ፡ ውበቴ [2X]

የማታረጀው ፡ ማትቀደደው
ሀሩር ፡ ሲመጣ ፡ ማትቀየረው
ዘላለማዊው ፡ ልብሴ ፡ የኔነቴ: ውበት ፡ ግርማ
ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ ነህ ፡ የክብር ፡ ሁሉ ፡ መደምደሚያ

    ዘላለማዊ ፡ ልብሴ ፡ ነህ ፡ ውበቴ [2X]

እንዳለ  ወልደጊዮርጊስ     7

ነፍሴ ፡ ተስፋ

ነፍሴ ፡ ተስፋ ፡ እያደረገችህ
    ምትዉልብህ ፡ ምታድርብህ
    ህያዉ ፡ ተስፋዬ
    ልቤ ፡ አንተን ፡ አምኖ ፡ ልቤ
    ልቤ ፡ ባንተ ፡ ፀና ፡ ልቤ [፪X] 

ጓዳዬን ፡ ሙላ ፡ አደባባዬን
ልኑር ፡ አንተን ፡ ስል ፡ ቀሪ ፡ ዘመኔን
ምንም ፡ አልሆንም ፡ አንተን ፡ ብያለሁ
የደህንነቴን ፡ እራስ ፡ ይዣለሁ

ልቤ ፡ ፀናልኝ ፡ አንተን ፡ በማመን
ፍጹም ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ የለብህ ፡ እንከን
ነፍሴ ፡ ትላለች ፡ ህያዉ ፡ ተስፋዬ
ከአዳኝ ፡ ወጥመድ ፡ መሸሸጊያዬ

    ነፍሴ ፡ ተስፋ ፡ እያደረገችህ
    ምትዉልብህ ፡ ምታድርብህ
    ህያዉ ፡ ተስፋዬ
    ልቤ ፡ አንተን ፡ አምኖ ፡ ልቤ
    ልቤ ፡ ባንተ ፡ ፀና ፡ ልቤ [፪X] 

አንተን ፡ ያደረገ ፡ መድህን ፡ አንተን ፡ ያደረገ ፡ ጥላ
ሆነህለት ፡ አየሁ ፡ እንጂ ፡ ክፉ ፡ እንዳይነካዉ ፡ ከለላ

እኔስ ፡ ኧረ ፡ እኔስ ፡ ካሉት ፡ ከለላ ፡ ካሉት ፡ አጥር
[እንደምትበልጥ ፡ አይቻለዉ ፡ እግዚአብሔር] [፪X]

እንዳለ  ወልደጊዮርጊስ     8

አትደክምም

አውቄአለሁ ሰምቻለሁ እኔ 
       እግዚአብሔር እግዚአብሔር 
        የዘላለም አምላክ የምድር ዳርቻ ፈጣሪ መሆንህን ፪x
         አትደክምም አትታክትም
         ማስተዋልህ አይመረመርም ፪x
            ኦ.ኦ.ኦ.ኦ. ዘላለም ዘላለም አምላክ ነህ አምላክ ነህ ፪x
         ኦ.ኦ.ኦ.ኦ. ዘላለም ዘላለም ገዢ ነህ ገዢ ነህ ፪x

   ፩/ከፍ ካልኩበት ፍፁም አልወርድም 
    በብርታቴ ላይ ፀሃይ አትጠልቅም 
     ያለ በሙሉ የለም ከስፍራው 
     ሸክላ ብርታቱ ተሰብሮ ከዳው
      አንተ ግን ጌታ ያው ሁሌ አንተ ነህ 
      ያለመናወጥ የምትኖር ከብረህ ፪x

          አትደክምም አትታክትም
         ማስተዋልህ አይመረመርም ፪x
           ኦ.ኦ.ኦ.ኦ. ዘላለም ዘላለም አምላክ ነህ አምላክ ነህ ፪x
         ኦ.ኦ.ኦ.ኦ. ዘላለም ዘላለም ገዢ ነህ ገዢ ነህ ፪x

    ፪/ያለአንተ የሆነ አንዳችም የለም 
    ማንም ራሱን ፈጥሮ አላገኘም 
     የጥንት የአሁኑ ፍጥረት በሙሉ 
     በአንተ ተገኘ ሆንከው መኖሩ 
      ሁሉም የሆነው ጌታ በአንተ ነው 
       ፈጣሪ አምላኬ አመልክሃለሁ ፪x

         አትደክምም አትታክትም
         ማስተዋልህ አይመረመርም ፪x
          ኦ.ኦ.ኦ.ኦ. ዘላለም ዘላለም አምላክ ነህ አምላክ ነህ ፪x
         ኦ.ኦ.ኦ.ኦ. ዘላለም ዘላለም ገዢ ነህ ገዢ ነህ ፪x

እንዳለ  ወልደጊዮርጊስ     9

ምን ፡ አሉ

ምን አሉ 2x አይባል
ምን አለ 2x ነው ምለው
2x 

ምሰማው የጌታዬን ድምፅ ነው
የምሰማው የጌታሄን ድምፅ ነው
2x 

አልሰጥም ጆሮዬን ለአለም
ጫጫታ ለወረደ ወሬ
የሀያሉ ጌታ ቃል ብቻ ይሰማል ሁሌ በሰፋሬ

ምን አሉን ትቼ ምን አለ እላለሁ 
የኢኔ ከፍታ የጌታ የጌታ ድምፅ ነው
2x

ጆሮን ከሰጡ ለሚባልው ሁሉ
ሩጫ ይቆማል ወደዱም ጠሉም
ይባላል እንጂ ጌታ ምን ይለል 
ድምፅ ደካማን አፅንቶ የቆማል

ምን አሉን ትቼ ምን አለ እላለዉ
የኔ ከፍታ የጌታ የጌታ ድምፅ ነው
2x

ምን አሉ 2x አይባልም
ምን አለ 2x ነው ምለው
2x
ምሰማው የጌታሄን ድምፅ ነው
የምሰማው የጌታሄን ድምፅ ነው
2x 

ሩጫውን ጫርሶ በአብ ቃኝ ተምቶ
ሚጠብቀኝ አለ ሽልማቴን ይዞ
አቆርጫ አልወጣም 
ወደ ጌታ አያላሁ
ድምፁን የሰማኛል 
በርግጥ ጨርሳላሁ

ምን አሉን ትቼ ምን አለ እላለው
የኔ ከፍታ የጌታ የጌታ ድምፅ ነው
2x

እንዳለ  ወልደጊዮርጊስ     10

ክብር ፡ ሁሉ

እንኮን ፡ ልመካ ፡ እንዲህ ፡ ነኝ ፡ ብዬ ፡ እኔ ፡ የእኔ ፡ ልል ፡ ቃል ፡ አስረዝሜ
ኔን ፡ አስጀምሮ ፡ የሚያስጨርሰኜ ፡ ከራሴ ፡ ምለው ፡ አንዳችም ፡ የለም 

አሁን ፡ የሆንኩትን ፡ መሆን ፡ የመቻሌ 
ጌታ ፡ በአንተ ፡ እኮነው ፡ አይደለም ፡ በእኔ

ክብር ፡ ሁሉ ፡ ለአንተይሁን # ፬

እኔ ፡ ለማለት ፡ __ቢሉልኝ ፡ ፡ ሰዎች ፡ ብጠራ ፡ 
ማንም ፡ አይገኝ ፡ በአሸዋ ፡ ላይ ፡ ቤቴን ፡ ስሥራ ፡ 
እርሱ ፡ ነው ፡ ስል ፡ ግን ፡ ተሰብሰቡና ፡ አዎ ፡ በሉልኝ 
 ይህን ፡ ላረገው ፡ ታማኙ ፡ ጌታ ፡ (ክብር ፡ አምጡልኝ) ፡ # ፰

ስሙኝ ፡ ወገኖች ፡ ይህን ፡ ስናገር ፡ ብሕይወቴ ፡ ላይ ፡ ለሆነው ፡ ነገር 
እንኳን ፡ ልታበይ ፡ እኔን ፡ ላበዛ ፡ ትንፋሽ ፡ መንገዱን ፡ ከፍሎ ፡ እንደገዛ 
ከቶ ፡ አልመካም ፡ እንዲያው ፡ በከንቱ ፡ ከእኔ ፡ ሳይሆን ፡ ሁሉ ፡ ነው ፡ በእርሱ 
እ ፡ የሚለውን ፡ ፊደል ፡ ጀምሬ ፡ ን ፡ ለመጨረስ ፡ ኃይል ፡ የለኝ ፡ እኔ

እያሉኝ ፡ ነው ፡ በአንተነው ፡ ጌታ 
ሁሉን ፡ አድርገህ ፡ የምታስመካኝ ፡ ሁንከኝ ፡ አለኝታ 

ክብር ፡ ሁሉ ፡ ለአንተይሁን # ፬

ኧረ ፡ ምንድ ፡ ነው ፡ ከእኔ ፡ ነው ፡ የምለው 
ኃይሌ ፡ ብርታቴ ፡ እጄ ፡ ያረገው 
ማበዛላቸው ፡ ብዙ ፡ እኔዎች 
ሁኑ ፡ ምላቸው ፡ በእኔ ፡ ክንዶች 
ምንም ፡ የለኝም ፡ የሚያስብለኝ ፡ እኔ 
ክብር ፡ ሚገባው ፡ ለአንተ ፡ ጌታዬ

እንኮን ፡ ልመካ ፡ እንዲህ ፡ ነኝ ፡ ብዬ ፡ እኔ ፡ የእኔ ፡ ልል ፡ ቃል ፡ አስረዝሜ
ኔን ፡ አስጀምሮ ፡ የሚያስጨርሰኜ ፡ ከራሴ ፡ ምለው ፡ አንዳችም ፡ የለም

ክብር ፡ ሁሉ ፡ ለአንተይሁን # ፬

እንዳለ  ወልደጊዮርጊስ     11

አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ

እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም (፪x)

አዝ፦ አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ
የሥምህ ፡ ሥልጣን ፡ ታላቅ ፡ ነው (፬x)

ከጣዖታት ፡ ዘንድ ፡ ፊቴን ፡ አዙሬ
ለአንተ ፡ ክብር ፡ ሆነልኝ ፡ መዝሙሬ

ስል ፡ አንተ ፡ እና ፡ ሥምህ ፡ ታላቅ ፡ ነው
ሌላ ፡ ቃላት ፡ መግላጫ ፡ ባጣ ፡ ነው (፪x)

አዝ፦ አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ
የሥምህ ፡ ሥልጣን ፡ ታላቅ ፡ ነው (፬x)

ቢሰለፉ ፡ አማልክት ፡ በተርታ
ካንዳቸውም ፡ መሳይ ፡ የለ ፡ ጌታ
እንደ : ስምህ: ነህ ፡ የሁሉ ፡ ገዢ
ዘመንህ ፡ ዕድሜ ፡ አይባልም ፡ ከዚህ

ልክ ፡ የለህም ፡ ወሰን ፡ የለህም
ልክ ፡ የለህም ፡ መጠን ፡ የለህም
በሰው ፡ ቋንቋ ፡ ከቶ ፡ አልገልጥህም (፪x)

ሥምህ ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ ለጠራው ፡ ሁሉ ፡ ሚሆን ፡ መዳኛ
ሥምህ ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ ለደካከመው ፡ ብርታት ፡ ማግኛ
አንተ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ በምንም ፡ ነገር ፡ ከቶ ፡ አትለካም
አንተ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ ዘመን ፡ አያልቅም ፡ የለብህ ፡ ድካም

እንዳለ  ወልደጊዮርጊስ     12

ጌታ ፡ ልዩ ፡ ነው

ነፍሴ ፡ ወደ ፡ ሕያው 
አምላክ ፡ ተጠማች [፪X]

ልረካህ ፡ ብል ፡ እህህ
በቃኝ ፡ ልል ፡ ብል ፡ እህህ
አልችልም ፡ ኢየሱስ ፡ ሚጠገብ ፡ እኮ ፡ አይደለም
  
    እሱ ልዩ ነው ልዩ [፪x]
    ጌታ ልዩ ነው ልዩ [፪x]

ለታላቅነቱ ፡ ለታላቅነቱ 
ምስጋናውን ፡ አምጡ [፪x]

እፎይ ፡ እረካው ፡ የልቤ ፡ ደርሷል
አሁን ፡ ለጌታ ፡ ምለው ፡ ምን ፡ ቀርቷል
ብዬ ፡ ደምድሜ ፡ ገና ፡ ስል ፡ ቁጭ
ብሶ ፡ ይፈልቃል ፡ የዜማው ፡ ምንጭ
ብዬ ፡ ነበረ ፡ እንደዚህ ፡ ብዙ 
ሚያቆም ፡ አይደለም ፡ የዜማው ፡ ወንዙ
ይሄን ፡ ስጨርስ ፡ ምለው ፡ ሌላ ፡ አለኝ 
ጌታ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ የሚያዘምረኝ

    እሱ ልዩ ነው ልዩ [፪x]
    ጌታ ልዩ ነው ልዩ [፪x]

ሌቤ ፡ የተመኘው ፡ ነገሬ ፡ ሳገኘው ፡ ደርሶ 
የውስጥ ፡ ርካታና ፡ ደስታ ፡ አይሰጥ ፡ ጨርሶ
ሁሉንም ፡ ነገር ፡ አይቼ ፡ ስልችት ፡ ሲለኝ
ዛሬም ፡ ዘላለም ፡ ማይሰለች ፡ አንድ ፡ ጌታ ፡ አለኝ

ከዉሃ ፡ ይልቅ ፡ እኔ ፡ ሚጠማኝ 
ከምግብ ፡ ይልቅ ፡ እኔ ፡ ሚርበኝ

 [የውስጤ ናፍቆት፡ ኢየሱስ [፪X]
የልቤ ናፍቆት፡ ኢየሱስ] [፪x]

    እሱ ልዩ ነው ልዩ [፪x]
    ጌታ ልዩ ነው ልዩ [፪x]

እንዳለ  ወልደጊዮርጊስ     13

አልፋ ፡ ኦሜጋ

አቤቱ ፡ ለቀዳሚነትህ ፡ ጥንት
ለኋላኛናትህ ፡ ፍጻሜ ፡ የለህ [፪x]

  አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ [፬X]
  
  አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ፊተኛ ፡ ኋለኛ [፬X]

ጌታ ፡ ዘመናትህ ፡ ዓማታትህ ፡ ቢቆጠሩ ፡ አያልቁም
ለአንተ ፡ ምን ፡ ቢበዙ ፡ የዕድሜ ፡ ገደብ ፡ ከቶ ፡ አይችሉም ፡ ሊሰጡህ
ዘመናትን ፡ አሳልፈህ ፡ አሳልፈህ 
አንተ ፡ ብቻ ፡ ትኖራለህ ፡ ትኖራለህ

    ዘላለማዊ ፡ ነህ
    ዘላለማዊ ፡ ነህ [፬X]

አናልፍም ፡ ያሉ ፡ አለፉ
አንሞትም ፡ ያሉትም ፡ ሞቱ
ኃያላን ፡ ለአንተ ፡ ሰገዱ
ኃይል ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው ፡ አሉ

የአንተ፡ አልፋ ፡ የአንተ ፡ ኦሜጋ
ሁሌ ፡ ጽኑ ፡ ነው ፡ መሽቶ ፡ ሲነጋ
መንግስትህ ፡ ቋሚ ፡ ዘላለማዊ
ሁሉ ፡ ሲያከትም ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ነዋሪ

    ዘላለማዊ ፡ ነህ
    ዘላለማዊ ፡ ነህ [፬X]

ጌታ ፡ እግዚአብሔር ፡ ሆይ
አንተ ፡ ያልነበርክበት ፡ ጊዜ
ለቅጽበት ፡ አልነበረም ፡ አይኖርም

  ስልጣንህ ፡ መንግስትህ ፡ ነው ፡ ከዘላለም [፬x]

እንዳለ  ወልደጊዮርጊስ     14

ምህረትህ

አዝ፦ ጌታ ፡ ምህረትህ ፡ ይግነንልኝ 
በድል ፡ ጨርሼ ፡ እቆማለሁ (፪x)
ጌታ ፡ ምህረትህ ፡ ይግነንልኝ
በድል ፡ ጨርሼ ፡ እቆማለሁ (፪x)

በዓይነ ፡ ህሊናዬ ፡ ዕሩቅ ፡ተጉⶴ 
ራሴን ፡አያለሁ ፡ ምርኩዜን ፡ይⶴ
የማይጸጽትን ፡ሕይወትን ፡ኖሬ
የጠራኸኝን ፡ አምለክ ፡ አክብሬ
ስል ፡ይታያኛል ፡ እፎይ ፡ተመስገን
ስለ ፡ ረዳኸኝ ፡በቃው ፡ ለዚች ፡ቀን
(ስል ፡ይታያኛል ፡እፎይ ፡ተመስገን
ስለ ፡ረዳኸኝ ፡በቃው ፡ ለዚች ፡ቀን)

አዝ፦ ጌታ ፡ ምህረትህ ፡ ይግነንልኝ 
በድል ፡ ጨርሼ ፡ እቆማለሁ (፪x)
ጌታ ፡ ምህረትህ ፡ ይግነንልኝ
በድል ፡ ጨርሼ ፡ እቆማለሁ (፪x)

አንድ ፡አንዴ ፡ እለላሁ ፡ ቶሎ ፡ አልፎልኝ 
የሽምግልናን ፡ ዕድሜን ፡ ባየሁኝ
ዝም ፡ ብዬ ፡ አይደለም ፡ እንዲህ ፡ ማለቴ
የቀኑን ፡ ክፋት ፡ ነው ፡ በማየቴ
የጉብዝናዬን ፡ ወራት ፡ ያዛቻው 
ሳሾፍ ፡ ስቀልድ ፡ አልለፋቸው
(የጉብዝናዬን ፡ ወራት ፡ ያዛቸው 
ሳሾፍ ፡ ስቀልድ ፡ አልለፋቸው)

አዝ፦ ጌታ ፡ ምህረትህ ፡ ይግነንልኝ 
በድል ፡ ጨርሼ ፡ እቆማለሁ (፪x)
ጌታ ፡ ምህረትህ ፡ ይግነንልኝ
በድል ፡ ጨርሼ ፡ እቆማለሁ (፪x)

የአንዳንዱን ፡ ቀን ፡ የሕይወት ፡ ቀጠሮ
እሮጦ ፡ ማለፍ ፡ ቢቻል ፡ ወይ ፡ በሮ
ይመኛል ፡ ልቤ ፡ እንዳላያቻው
ባመልጥ ፡ ብሰወር ፡ ከክፋታቻው
ግን ፡ አይቻልም ፡ እስካለው ፡ በምድር
መሽቶ ፡ ሲነጋ ፡ ማየቴ ፡ አይቀር
ለእኔ ፡ አለ ፡ እንጂ ፡ የአንተ ፡ ጥበቃ
ውርደት ፡ እያየ ፡ ለክብር ፡ ሚያበቃ

አዝ፦ ጌታ ፡ ምህረትህ ፡ ይግነንልኝ 
በድል ፡ ጨርሼ ፡ እቆማለሁ (፪x)
ጌታ ፡ ምህረትህ ፡ ይግነንልኝ
በድል ፡ ጨርሼ ፡ እቆማለሁ (፪x)

  • facebook
  • twitter
  • linkedin

©2019 by My Site. Proudly created with Wix.com

bottom of page