
በረከት ተስፋዬ
Mezmur
ስንድቄ
ይሄ ፡ ነው ፡ ንጉሤ
አነሱ
ስሰማው
መንፈስህ
አቤት ፡ ደግነት
ዘምራለሁ
ሁሉን ፡ ቀድሜዋለሁ
ባለውለታዬ
ጌታን ፡ አገኘሁ
ከየት ፡ እንደመጣሁ
መዳኛ
በረከት ተስፋዬ 1
ስንድቄ
መዝሙሬ ፡ አንተ ፡ ነህ
መልዕክቴ ፡ አንተ ፡ ነህ
ሰንደቄ ፡ ጌታ ፡ አንተ ፡ ነህ
ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ
ታይልኝ ፡ ታይልኝ
በመዝሙሬ ፡ ላይ ፡ ግነንልኝ
ዓይኖረኝ ፡ በቃ ፡ ሌላ ፡ እርዕስ
ደምቀህ ፡ ታይልኝ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
አርማዬ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ መታወቂያዬ
ዘምርሃለው ፡ ዘወትር ፡ ጌታዬ
ክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ የለህም ፡ አቻ
እቀኛለሁኝ ፡ ስለአንተ ፡ ብቻ
ሌላ ፡ መዝሙር ፡ ዓይኖረኝ
አንተ ፡ ብቻ ፡ ታይልኝ
ወሰንኩኝ ፡ ላልገኝ ፡ ለሌላዉ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መዝሙሬ ፡ የተገባዉ
መዝሙሬ ፡ አንተ ፡ ነህ
መልክቴ ፡ አንተ ፡ ነህ
ሰንደቄ ፡ ጌታ ፡ አንተ ፡ ነህ
ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ
ታይልኝ ፡ ታይልኝ
በመዝሙሬ ፡ ላይ ፡ ግነንልኝ
ዓይኖረኝ ፡ በቃ ፡ ሌላ ፡ እርዕስ
ደምቀህ ፡ ታይልኝ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
በረከት ተስፋዬ 2
ይሄ ፡ ነው ፡ ንጉሤ
ሰው ፡ ያልቻለውን ፡ የሚችለው ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
የተዘጋውን ፡ ማህተም ፡ የፈታ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ
እልፍ ፡ ኣላፋት ፡ ቅዱስ ፡ እያሉ ፡ ሚሰግዱለት
ግርማዊነቱ ፡ ህያው ፡ ንጉስ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
ወንበሩ ፡ በሰው ፡ የተደፈረ
ግርማዊ ፡ አይባል ፡ ሞቶ ፡ የቀረ
የእውነት ፡ ግርማዊ ፡ አንድ ፡ ንጉስ
ሞትን ፡ ያሸነፈ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
ከሞት ፡ ተነሳ (ኢየሱስ) (፪x)
መቃብሩን (ኢየሱስ) ፡ ባዶ ፡ አደረገው (ኢየሱስ)
የይሁዳ ፡ ነገድ (ኢየሱስ) ፡ ሞአ ፡ አንበሳው (ኢየሱስ)
አንበሳው ኢየሱስ(፬x)
ከጥንት ፡ ጀምሮ ፡ ያለ ፡ የነበረ
ዙፋኑ ፡ ጽኑ ፡ ነው ፡ ከቶ ፡ ያልተደፈረ
ጉልበት ፡ ያለው ፡ ሁሉ ፡ ሚንብረከክለት
አጋንንት ፡ ለስሙ ፡ ሚንቀጠቀጡለት
እርሱ ፡ የዘጋውን ፡ የሚከፍት ፡ የለ
የከፈተውን ፡ ሚዘጋ ፡ የለ
በሰማይ ፡ በምድር ፡ የሌለው ፡ አቻ
ንጉሰ ፡ ነገስት ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ
ፊቱ ፡ እንደ ፡ ፀሐይ (ኢየሱስ) ፡ የሚያበራ ፡ ነው (ኢየሱስ)
ከበረዶ ፡ ይልቅ (ኢየሱስ) ፡ ጸጉሩ ፡ ነጭ ፡ ነው (ኢየሱስ)
ዓይኖቹ ፡ እንደሳት (ኢየሱስ) ፡ ነበልባል ፡ ናቸው (ኢየሱስ)
እንደ ፡ ብዙ ፡ ውሆች (ኢየሱስ) ፡ ድምጹ ፡ አስፈሪ ፡ ነው (ኢየሱስ)
ዮሐንስ ፡ አለ ፡ (ኢየሱስ) ፡ በክብር ፡ ቢያየው ፡ (ኢየሱስ)
ፊቱ ፡ ወደኩኝ (ኢየሱስ) ፡ እንደ ፡ ሞተ ፡ ሰው (ኢየሱስ)
ይሄ ፡ ነው ፡ ንጉሥ (ኢየሱስ) (፪x)
እንዲህ ፡ ነው ፡ ንጉሥ (ኢየሱስ) (፪x)
አንበሳው (ኢየሱስ) (፪x)
ይገባዋል (ኢየሱስ)
ንጉስ ፡ መባል ፡ የተገባው ዝጉን ፡ ማህተም ፡ የፈታው
ለሌላ ፡ አንሰጥም ፡ ክብሩን ሞትና ፡ ትንሳኤውን
መባል ፡ ያለበት ፡ ሞአንበሳ ሞትን ፡ ድል ፡ አድርጎ ፡ ለተነሳ
ሰማይ ፡ ያረገ ፡ በደመና ዳግም ፡ ሚመጣ ፡ እንደገና
ይሄ ፡ ነው ፡ ንጉሥ (ኢየሱስ) (፬x)
አንበሳው ፡ ኢየሱስ (፪x)
ኢየሱስ
የደስታዬን ፡ ዕልልታ (፪x) ፡ ንጉሥ ፡ ለሆነው ፡ ፡ ጌታ
የደስታዬን ፡ ዕልልታ (፪x) ፡ አስማለሁ ፡ ለጌታ
የደስታዬን ፡ ጩኸት (፪x) ፡ ለንጉሠ ፡ ነገሥት
የደስታዬን ፡ ጩኸት (፪x) ፡ እስቲ ፡ ልጩኽለት
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ እስቲ ፡ ናልኝ ፡ ኢየሱስን ፡ አክብርልኝ
የውስጤ ፡ ጥማት ፡ መሻቴ ፡ ወልድ ፡ ሲከብር ፡ በሕይወቴ
አምልኮ ፡ የሚያምርብኝ ፡ ጎኔ ፡ ስትቆምልኝ
በመውጣት ፡ መግባቴ ፡ ላይ ፡ ንጉሳችን ፡ ሁን ፡ የበላይ
ሁንልኝ ፡ የበላይ (፬x)
ሁንልኝ ፡ የበላይ (፬x)
የበላይ (፬x) ፡ የበላይ (፬x)
የበላይ
የበላይ ፡ እህህህም ፡ የበላይ
በረከት ተስፋዬ 3
አነሱ
በክርስቶስ ፡ ኢየሱስ (፫x)
ተወለድኩ ፡ ከመንፈስ (፫x)
ዳግም ፡ ዉልደት ፡ አግኝቻለው (፫x)
የጨዋዪቱ ፡ ልጅ ፡ ነኝ ፡ የባሪያዪቱ ፡ አይደለሁም
በተስፋ ፡ ቃሉ ፡ ወልዶ ፡ የርስቱ ፡ ወራሽ ፡ አረገኝ
በክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ወራሽ ፡ ነኝ
ቃሉ ፡ ነህ ፡ የሚለኝን ፡ ልክ ፡ እንደዛው ፡ ነኝ
አነሱ ፡ ምድር ፡ ሰማይ (፫x)
እርስቴን ፡ እግዚአብሔርን ፡ ሳይ (፫x)
ፈልጌያቸው ፡ አጣኋቸው (፪x)
ሳስተያያቸው
መልካም ፡ አደረገ ፡ አብ ፡ አባት ፡ ከላይ
እኔነቴን ፡ ሳይሆን ፡ ልጁን ፡ በእኔ ፡ ሲያይ
ልጅ ፡ መሆኔ ፡ ሳያንሰኝ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ወራሽ ፡ ነኝ
አነሱ ፡ ምድር ፡ ሰማይ (፫x)
እርስቴን ፡ እግዚአብሔርን ፡ ሳይ (፫x)
ፈልጌያቸው ፡ አጣኋቸው (፪x)
ሳስተያያቸው
በረከት ተስፋዬ 4
ስሰማው
ስሰማዉ (፫x) ፡ ስሰማው (፫x)
የማይሰለቸኝ ፡ የማይሰለቸኝ
እየሱሴ ፡ የአንተ ፡ ስም ፡ ነዉ ፡ እወደዋለሁኝ (፪x)
ስላንተ ፡ በየዕለቱ ፡ በየማታዉ
ስላንተ ፡ በየዕለቱ ፡ በየማታዉ
መስማት ፡ አይሰለቸኝ (፪x)
ተሰበኬ (፪x) ፡ ሰምቼ (፪x)
ጆሮዬ ፡ ያልጠገበዉ ፡ ያንተን ፡ ስም ፡ ነዉ (፪x)
ኢየሱስ ፤ ኢየሱስ ፤ ኢየሱስ ፤ ኢየሱስ (፪x)
የሚጣፍጠኝ ፡ ስም ፡ ኢየሱስ
እኔ ፡ ምወደዉ ፡ ስም ፡ ኤየሱስ
የምታዘዘዉ ፡ ስም ፡ ኢየሱስ
እኔ ፡ ምወደዉ ፡ ስም ፡ ኢየሱስ
የከበረ ፡ ስም ፡ የተቀባ ፡ ስም
የምወደዉ ፡ ስም ፡ ምኖርለት ፡ ስም
የከበረ ፡ ስም ፡ እሳት ፡ ያለዉ ፡ ስም
የምወደዉ ፡ ስም ፡ ምኖርለት ፡ ስም
እጠራዋለሁ ፡ ኢየሱስ (፰x)
ስሙ ፡ የጸና ፡ ግንብ ፡ ነዉ (፫x)
ስሙ ፡ የጸና ፡ ግንብ ፡ ነዉ (፫x)
ጻድቅ ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ ሮጦ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ይላል
የጌታን ፡ ስም ፡ የሚጠራ ፡ እርሱ ፡ ይድናለል (፪x)
ስሰማዉ (፫x) ፡ ስሰማው (፫x)
የማይሰለቸኝ ፡ የማይሰለቸኝ
እየሱሴ ፡ የአንተ ፡ ስም ፡ ነዉ ፡ እወደዋለሁኝ (፪x)
ስላንተ ፡ በየዕለቱ ፡ በየማታዉ
ስላንተ ፡ በየዕለቱ ፡ በየማታዉ
መስማት ፡ አይሰለቸኝ (፪x)
በረከት ተስፋዬ 5
መንፈስህ
እንጨት ፡ እና ፡ ውኃ ፡ በሌለበት ፡ ቦታ
ናፈቅከኝ ፡ ጌታ ፡ ናፈቅከኝ ፡ ጌታ (፪x)
ትርጉም ፡ ባለበት ፡ የውኃ ፡ ጠብታ
ግን ፡ ነፍሴ ፡ ጮኽች ፡ አንተን ፡ ተጠምታ
አምላኬ ፡ አንተ ፡ ዘንድ ፡ እገሰግሳለው
ክብርህን ፡ ለማየት ፡ እናፍቃለው (ኦኦው)
መንፈስህን (፬x)
ወደዋለው ፡ መንፈስህን
ተጠምቻለው ፡ መንፈስህን
መንፈስህን (፬x)
ወደዋለው ፡ መንፈስህን
ተጠምቻለው ፡ መንፈስህን
ህልውናህ ፡ ለእኔ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው
መገኘትህ ፡ ለእኔ ፡ የነፍሴ ፡ ደስታ ፡ ነው
እጠማሃለው (፪x)
እወድሃለው (፪x)
ስንዘምር ፡ አንተን ፡ ስንጠራ
በጉባያችን ፡ ክብርህ ፡ ሲገባ
ያለሁ ፡ መሰለኝ ፡ መንግሥተ ፡ ሰማይ
መገኘትህን ፡ በመንፈሴ ፡ ሳይ (፪x)
በረከት ተስፋዬ 6
አቤት ፡ ደግነት
እውነትነቱን ፡ በመስቀል ፡ ላይ
መቶ ፡ አለቃው ፡ ጌታዬን ፡ ቢያይ
ተንበረከከ ፡ ሰገደለት
ነካው ፡ የጌታ ፡ ቅንነት
እንኳን ፡ አሁን ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ብሎ
አሸንፎአል ፡ ተንጠልጥሎ
ሳያስፈራራ ፡ ሰው ፡ አንበርካኪ
እንደእርሱ ፡ የለም ፡ ፍቅር ፡ ሰባኪ
አቤት ፡ ደግነት ፡ ቸርነቱ
ለሰው ፡ ያሳየው ፡ ምህረቱ (፮x)
ፍቅር ፡ ምህረቱን ፡ የቀመሱቱ
ውበቱን ፡ ያዩ ፡ ሐዋሪያቱ
ስለእርሱ ፡ ኖረው ፡ መረጡ ፡ ሞት
ለፍቅሩ ፡ ሆኑ ፡ ሰማዕታት
ተነክተው ፡ በምህረቱ
ተነክተው ፡ በቸርነቱ
ነክቶአቸው ፡ ገርነቱ
ነክቶአቸው ፡ የዋህነቱ
የቱ ፡ ጀግና ፡ ነው ፡ እጁን ፡ ያልሰጠ
የሱስን ፡ አይቶ ፡ ያልደነገጠ
ልከተልህ ፡ ያላለ ፡ ማነው
የኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ አሸናፊ ፡ ነው
ከጫፍ ፡ ጫፍ ፡ ስንቱን ፡ ማረከ
በፍቅሩ ፡ አንበረከከ
ምን ፡ ዓይነት ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ እንጃ
ወደደንው/ሰገድን ፡ያለ፡ ጠመንጃ (፪x)
አቤት ፡ትህትና ፡አይ ፡ቅንነት
ሰውን፡ ያስተማረ ፡ኖሮ ፡በሕይወት
የሚሸጠውን፡ እግር ፡ ያጠበ
ሩህሩህ ነው ጌታ፡ ፍቅር ፡ያነገበ
ይህንን ፡ ጌታ ፡ የምትወዱት
አስቲ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ኢየሱስን ፡ እንዲህ ፡ በሉት (፪x)
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ እንዳንተ ፡ ያለ
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ አለ (፬x)
በረከት ተስፋዬ 7
ዘምራለሁ
የኢየሱስ ፡ ደም ፡ የፈሰሰው
እስከ ፡ መስቀል ፡ የታዘዘው
ይወደኛል የዉነት ፡ ሰጠኝ ፡ ነፍሱን
ኦኦኦ
ዘምራለው ፡ ዘምራለው ፡ ለመድኃኒቴ (፪x)
ሞት ፡ የተገባኝ ፡ እኔ ፡ ነበርኩኝ
በበደሌ ፡ ምክንያት ፡ ከአምላክ ፡ የራቅኩኝ
ሞተልኝ ፡ ሞቴን ፡ ሸለመኝ ፡ የእርሱን
ኑሮውን ፡ አኖረኝ ፡ የእኔን ፡ ሞት ፡ ሞተልኝ
ለእኔ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ነው (፪x)
ኦ ፡ ለእኔ ፡ ነው (፪x) ኢየሱስ ፡ የሞተው
በመስቀል ፡ ሞት ፡ ተዋረደልኝ
እንደጠቦት ፡ የታረደልኝ
መርገሜን ፡ የወሰደው ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ዘምራለው ፡ ዘምራለው ፡ ለመድኃኒቴ (፬x)
በረከት ተስፋዬ 8
ሁሉን ፡ ቀድሜዋለሁ
የደስታዬ ፡ ምንጭ ፡ አንተ ፡ ነህ (፪x)
ነገር ፡ ቢሞላ ፡ ነገር ፡ ባይሞላ
የደስታዬ ፡ ምንጭ ፡ አንተ ፡ ነህ
የሰላሜ ፡ ምንጭ ፡ አንተ ፡ ነህ (፪x)
ነገር ፡ ቢሞላ ፡ ነገር ፡ ባይሞላ
የሰላሜ ፡ ምንጭ ፡ አንተ ፡ ነህ
ጥበበኛዋ ፡ ሴት ፡ ቀዝቃዛውን ፡ ክረምት
ሩቅ ፡ አይታ ፡ ልብሷን ፡ ሰፋች ፡ መከራውን ፡ ቀደመች
እኔም ፡ እንደ ፡ እሷ ፡ ሁሉን ፡ ቀድምያለሁ
በእየሱስ ፡ ተደስቻለሁ (፪x)
ሃዘንን ፡ ቀድሜዋለው ፡ ጭንቀትን ፡ ቀድሜዋለው
ተድላን ፡ ቀድሜዋለው ፡ ስኬትን ፡ ቀድሜዋለው
የደስታዬ ፡ ምንጭ ፡ አንተ ፡ ነህ (፪x)
ነገር ፡ ቢሞላ ፡ ነገር ፡ ባይሞላ
የደስታዬ ፡ ምንጭ ፡ አንተ ፡ ነህ
የሰላሜ ፡ ምንጭ ፡ አንተ ፡ ነህ (፪x)
ነገር ፡ ቢሞላ ፡ ነገር ፡ ባይሞላ
የሰላሜ ፡ ምንጭ ፡ አንተ ፡ ነህ
የተቀደመ ፡ ነው ፡ የቀረው ፡ ዘመኔ
የዘላለም ፡ ደስታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆኖኝ ፡ ለእኔ
ቀድሜ ፡ ተደስቻለው (፪x)
በኢየሱስ ፡ ተደስቻለው (፪x)
እንደ ፡ ወንዝ ፡ ነው ፡ ሰላሜ (፫x)
ይፍለቀለቃል ፡ ከውስጤ
አይቋረጥም ፡ ሰላሜ (፫x)
ይፍለቀለቃል ፡ ከውስጤ
የደስታዬ ፡ ምንጭ ፡ አንተ ፡ ነህ (፪x)
ነገር ፡ ቢሞላ ፡ ነገር ፡ ባይሞላ
የደስታዬ ፡ ምንጭ ፡ አንተ ፡ ነህ
የሰላሜ ፡ ምንጭ ፡ አንተ ፡ ነህ (፪x)
ነገር ፡ ቢሞላ ፡ ነገር ፡ ባይሞላ
የሰላሜ ፡ ምንጭ ፡ አንተ ፡ ነህ
ደስታ ፡ እና ፡ ሃዘኔ ፡ እኩያ ፡ ነበሩ
በልኬት ፡ ቁመና ፡ የሚፎካከሩ
ኢየሱስ ፡ ግን ፡ የሰጠኝ ፡ ደስታ
አይስተካከል ፡ ከሁኔታ
አባቴ ፡ የስጠኝ ፡ ደስታ
አይስተካከል ፡ ከሁኔታ
እንደ ፡ ወንዝ ፡ ነው ፡ ሰላሜ (፫x)
ይፍለቀለቃል ፡ ከውስጤ
እንደ ፡ ወንዝ ፡ ነው ፡ ሰላሜ (፫x)
ይፍለቀለቃል ፡ ከውስጤ
የደስታዬ ፡ ምንጭ ፡ አንተ ፡ ነህ
አንተ ፡ ነህ
በረከት ተስፋዬ 9
ባለውለታዬ
ወረቀት ፡ ብዕሬን ፡ አገናኘሁኝ
ስለጌታ ፡ ውለታ ፡ መጻፍ ፡ አሰኘኝ
የትኛውን ፡ ጽፌ ፡ የቱን ፡ ልተወው
የምለውን ፡ ባጣ ፡ እንዲህ ፡ ልበለው ፡ ልበለው
ባለውለታዬ ፡ ነው ፡ ጌታዬ (፬x)
ውለታ ፡ አለብኝ ፡ የማልመልሰው
የእግዚአብሄር ፡ ልጅ ፡ ለእኔ ፡ የሰራው
ስለ ፡ ኢየሱስ ፡ ሰፊ ፡ ጊዜ ፡ ያሻኛል
እንኳን ፡ ቀኑ ፡ ዘላለም ፡ ያንሰኛል
ታሪክ ፡ የሌለውን ፡ ባለታሪክ
ጠላት ፡ የሆንኩት ፡ ወዳጅ ፡ አረክ
አሳዳጅ ፡ የሆንኩትን ፡ ነካኽኝና
በቅዱሳኑ ፡ ፊት ፡ አቆምከኝና
ዘምር ፡ አልከኝ (፬x)
በስንኝ ፡ ቋጠሮ ፡ ችዪ ፡ ላልሰንቅ
ጠልቄ ፡ ባስብም ፡ አቅሜ ፡ እስኪያልቅ
አወይ ፡ በትንሿ ፡ በዚች ፡ ወረቀት
ጭሬ ፡ አልጨርሰው ፡ የሱን ፡ ሰጪነት ፡ ለጋስነት
መካኒቱ ፡ ሰባት ፡ ወለደች
ሳራም ፡ በእርጅና ፡ ጸነሰች
ሙሴን ፡ በጥበብ ፡ አሳደገ
ምስኪኑን ፡ ዳዊት ፡ ንጉሥ ፡ አደረገ
እንደዚህ ፡ ነው ፡ የኢየሱስ ፡ ስራ
አይጨረስ ፡ ሁሌም ፡ ቢወራ
እኔም ፡ አለኝ ፡ የምለው
አግኝቶኛል ፡ ውለታው
ባለውለታዬ ፡ ነው ፡ ጌታዬ (፬x)
ውለታ ፡ አለብኝ ፡ የማልመልሰው
የእግዛብሄር ፡ ልጅ ፡ ለእኔ ፡ የሰራው
ስለ ፡ ኢየሱስ ፡ ሰፊ ፡ ጊዜ ፡ ያሻኛል
እንኳን ፡ ቀኑ ፡ ዘላለም ፡ ያንሰኛል
ብዙ ፡ ነው ፡ የሱ ፡ ውለታ
ሳስበው ፡ ጥዋት ፡ እና ፡ ማታ
ግርም ፡ ይለኛል ፡ ድንቅ ፡ ይለኛል ፡ ቃላት ፡ ያጥረኛል
በምን ፡ ቋንቋ ፡ ነው ፡ በምን ፡ አንደበት
የምገልጸው ፡ የሱን ፡ በጐነት (፪x)
በረከት ተስፋዬ 10
ጌታን ፡ አገኘሁ
ተጭኖብኝ ፡ የማልችለውን
የሞት ፡ ፍርሀት ፡ አርጎኝ ፡ ምስኪን
መች ፡ አገዝኝ ፡ የእኔነት ፡ ካባዬ
አልቆ ፡ ነበር ፡ የመኖር ፡ ተስፋዬ
ግን ፡ አንድ ፡ ቀን ፡ ወንጌል ፡ ሰማሁኝ
ይታደጋል ፡ ያድናል ፡ ሲሉኝ
በቅንነት ፡ እጄን ፡ አነሳሁኝ
የዛች ፡ ለት ፡ ጌታን ፡ አገኘሁኝ
አዲስ ፡ ነገር ፡ የዛች ፡ ለት ፡ ሆነ (፪x)
በመንፈሴ ፡ ሰላም ፡ ሰፈነ (፪x)
አፈሰሰው ፡ በልቤ ፡ ደስታ (፪x)
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ የሰላም ፡ ጌታ (፪x)
በአገር ፡ በሰፈሩ ፡ እታማ ፡ ጀመረ
የእናት ፡ እና ፡ የአባቱን ፡ ሃይማኖት ፡ ቀየረ
ይህን ፡ ያንን ፡ ብለው ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ተነሱ
እኔ ፡ የቀመስኩትን ፡ ምነው ፡ በቀመሱ
ኢየሱስ ፡ ብቸኛ ፡ አማራጭ ፡ የሌለው
ወደ ፡ ሰማይ ፡ መግብያ ፡ ብቸኛ ፡ መንገድ ፡ ነው
ያዳነኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
የሞተልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
በመስቀል ፡ ላይ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
የተወጋልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ዋጋ ፡ ከፍሎ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
በደም ፡ ገዛኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ከጻድቃን ፡ ጋር ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
የቀላቀለኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
መዘበቻ ፡ አርጓት ፡ ነፍሴን ፡ ሰይጣን ፡ ክፉ ፡ አይራራ ፡ አያዝን
ከሱ ፡ ለማምለጥ ፡ ብዙ ፡ ጣርኩኝ ፡ ግን ፡ አልቻልኩኝ
በዚህ ፡ ሁኔታ ፡ ወንጌል ፡ ሰማሁኝ ፡ እየሱስን ፡ ተገናኘሁኝ
ሰው ፡ መሆኔን ፡ የወደድኩት ፡ ያየሁት ፡ ለት
የልጅነትን ፡ ሥልጣንን ፡ ሰጠኝ ፡ ሥልጣን ፡ ያሳደደኝን ፡ አሳደድኩኝ ፡ አሳደድኩኝ
የበቀል ፡ ቅባት ፡ እራሴን ፡ ቀባኝ ፡ እራሴን ፡ ቀባኝ
ያስጨነቀኝን ፡ አስጨነኩኝ ፡ አስጨነኩኝ
እናንተ ፡ ደካሞች ፡ ሸክማቹህ ፡ ከባድ
ወደ ፡ እኔ ፡ ኑ ፡ ያለ ፡ ይሄ ፡ ሰውን ፡ ወዳጅ
ያሳረፈኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ሰው ፡ ያደረገኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ያከበረኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ያዘመረኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ዋጋ ፡ ከፍሎ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
በደም ፡ ገዛኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ከጻድቃን ፡ ጋር ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
የቀላቀለኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
በረከት ተስፋዬ 11
ከየት ፡ እንደመጣሁ
መነሻ ፡ ስፍራዬን ፡ አስታውሰዋለሁ
ከየት ፡ እንዳነሳኸኝ ፡ መች ፡ እዘነጋዋለሁ
ፀጋህ ፡ በዝቶልኝ ፡ ነው ፡ ብሩህ ፡ ቀን ፡ ማየቴ
እጅህ ፡ ደግፎኝ ፡ ነው ፡ ያማረው ፡ ሕይወቴ
ያማረው ፡ ሕይወቴ (፪x)
ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ የሰመረው ፡ ያማረው ፡ ሕይወቴ
ትርጉም ፡ ያገኘሁት ፡ ለመኖሬ
ስለረዳኸኝ ፡ ነው ፡ እንዲህ ፡ መዘመሬ
ከየት ፡ እንደመጣሁ ፡ አስታውሰዋለሁ
እራሴን ፡ አውቃለሁ
የድሮው ፡ አድራሻዬን ፡ መች ፡ እረሳዋለሁ
ለሚያየኝ ፡ በእራሴ ፡ ብቁ ፡ ሰው ፡ እመስላለሁ
ግን ፡ እንዲህ ፡ መቆሜ ፡ ከአንተ ፡ የተነሳ ፡ ነው
ኦ ፡ ከየት ፡ እንደመጣሁ ፡ እራሴን ፡ አውቃለሁ
ለሚያየኝ ፡ በእራሴ ፡ ብቁ ፡ ሰው ፡ እመስላለሁ
ግን ፡ እንዲህ ፡ መቆሜ ፡ ከአንተ ፡ ይተነሳ ፡ ነው
ከየት ፡ እንደመጣሁ ፡ አስታውሰዋለሁ
እራሴን ፡ አውቃለሁ
የድሮው ፡ አድራሻዬን ፡ መች ፡ እረሳዋለሁ
ለሚያየኝ ፡ በእራሴ ፡ ብቁ ፡ ሰው ፡ እመስላለሁ
ግን ፡ እንዲህ ፡ መቆሜ ፡ ከአንተ ፡ የተነሳ ፡ ነው
ከአንተ ፡ የተነሳ ፡ ነው (፪x)
ለሚያየኝ ፡ በእራሴ ፡ ብቁ ፡ ሰው ፡ እመስላለሁ
ለሚያየኝ ፡ በእራሴ ፡ ብቁ ፡ ሰው ፡ እመስላለሁ
በረከት ተስፋዬ 12
መዳኛ
አዝ፦ መዳኛ ፡ ነህ ፡ መዳኛ (፪x)
ለተረሳው ፡ ሰው ፡ ጓደኛ
መዳኛ ፡ ነህ ፡ መዳኛ
አባቴ ፡ ነህ ፡ አባቴ (፪x)
አሳደከኝ ፡ ከልጅነቴ
አባቴ ፡ ነህ ፡ አባቴ (፪x)
ህልመኛው ፡ ተሽጦ ፡ ለግብፃዊ ፡ ቤት
አገልጋይ ፡ እንዲሆን ፡ ለረጅም ፡ ዓመት (፪x)
ሲመላለስ ፡ ሳለ ፡ በታማኝነት
በሀሰት ፡ ወንጅለው ፡ ከወይኒ ፡ ጣሉት (፪x)
ለመልካም ፡ ሆነለት ፡ አንተን ፡ በማክበሩ
ህልሙ ፡ እውን ፡ ሆነ ፡ ወጣ ፡ በመምበሩ (፪x)
ሰው ፡ ሳያይ ፡ በጓዳ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ፈሪ
መሆኑ ፡ አይቀርም ፡ ተፅዕኖ ፡ ፈጣሪ (፪x)
የተጣለን ፡ ምታነሳ ፡ ለምስኪኑ ፡ ምትሳሳ
የታሰረን ፡ የምትፈታ ፡ የደህንነት ፡ ጌታ (፪x)
አዝ፦ መዳኛ ፡ ነህ ፡ መዳኛ (፪x)
ለተረሳው ፡ ሰው ፡ ጓደኛ
መዳኛ ፡ ነህ ፡ መዳኛ
አባቴ ፡ ነህ ፡ አባቴ (፪x)
አሳደከኝ ፡ ከልጅነቴ
አባቴ ፡ ነህ ፡ አባቴ (፪x)
መከራው ፡ ስቃዩ ፡ ሲያልፍ ፡ በሕይወቴ
ከጐኔ ፡ አልተለየህ ፡ ኢየሱስ ፡ ረዳቴ ፡ ኢየሱስ ፡ አባቴ
እንዳያልፍ ፡ አለፈ ፡ ያ ፡ ሁሉ ፡ መከራ
ሃሩር ፡ ተሻገርኩኝ ፡ ከጌታዬ ፡ ጋራ ፡ ከኢየሱሴ ፡ ጋራ
የበረሃው ፡ ፀሐይ ፡ እንዳያቃጥለኝ
ደመናን ፡ አዞልኝ ፡ ጥላ ፡ አደረገልኝ (፪x)
እባብ ፡ እና ፡ ጊንጡ ፡ ነድፎ ፡ እንዳያስቀረኝ
ከፊቴ ፡ እየወጣ ፡ እረጋገጠልኝ (፪x)
አዝ፦ መዳኛ ፡ ነህ ፡ መዳኛ (፪x)
ለተረሳው ፡ ሰው ፡ ጓደኛ
መዳኛ ፡ ነህ ፡ መዳኛ
አባቴ ፡ ነህ ፡ አባቴ (፪x)
አሳደከኝ ፡ ከልጅነቴ
አባቴ ፡ ነህ ፡ አባቴ (፪x)