
ሀና ተክሌ
Mezmur
ኢየሩሳሌም
ተመሥገን
ዝጋብኝ
የዘለዓለም ፡ ፈጣሪ
ደም ፡ ተከፍሎበታል
የሮጡለትን ፡ ያዩታል
ያዛኝ ፡ ያለህ
ሰላም ፡ ነው
ወቅት ፡ እንዳታበላሽ
በጉባኤው ፡ መሃል
ያለ ፡ ምክንያት
ድሮዬን ፡ አልደግምም
ፍሰሃዬ
በፀሎት
ቤተ ፡ ሰሪ
ሀና ተክሌ 1
ኢየሩሳሌም
ከሚያስፈራው ፡ ከድቅድቁ ፡ ጨለማ
ወደሚደነቅ ፡ የብርሃን ፡ ከተማ
ሄደናል ፡ ተዘዋውረናል ፡ በዚያ ፡ የለንም
ዳግም ፡ ከዚያ ፡ ከሞት ፡ ሰፈር ፡ አንገኝም
ከምስራቅ ፡ ከምዕራብ ፡ ከደቡብ ፡ ከሰሜን
በብርሃኑ ፡ ብርሃን ፡ እያየን
ከነገድ ፡ ከዘር ፡ ቋንቋ ፡ ተዋጅተን
በአንድነት ፡ ለኢየሱስ ፡ እንዘምራልን
አባባት ፡ እያልን ፡ የምንኖርበት
የልጅነትን ፡ ስልጣን ፡ ሰጥቶናል
የብርሃን ፡ ዘር ፡ ምርጥ ፡ ዜጋ
በኢየሱስ ፡ በኢየሱስ ፡ አግኝተናል
አዝ፦ ኢየሩሳሌም (፪x) ፡ እንገባለን
ዘላልም ፡ በዚያ ፡ ዘለዓለም ፡ እንዘምራለን
ሃሌሉያ ፡ ሃሌ ፡ ሃሌ (፫x) ፡ ኢየሱስ
ሃሌሉያ ፡ ኢየሱስ
ሃሌሉያ ፡ ሃሌ ፡ ሃሌ (፫x) ፡ ኢየሱስ
ሃሌሉያ ፡ ኢየሱስ
ሀና ተክሌ 2
ተመሥገን
አግዘኝ ፡ ደግፈኝ ፡ ብዬ ፡ ነበረ
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ሰማኸኝ ፡ ስለቴም ፡ ሰመረ
ብዬ ፡ እልሃለው ፡ እንደገና
በአዲስ ፡ ዝማሬ ፡ በአዲስ ፡ ዜማ
የአየሁትን ፡ በዓይኔ ፡ አይቻለሁ
እጅህን ፡ በብዙ ፡ አይቻለሁ
ምሥጋናዬ ፡ በፊትህ ፡ ያርግልኝ
አምልኮዬ ፡ በፊትህ ፡ ይፍሰስልኝ
ዝማሬ ፡ በፊትህ ፡ ሞገስ ፡ ያግኝልኝ
አንተ ፡ አይደለህም ፡ ወይ ፡ ረዳቴ
በጭንቅ ፡ ዘመን ፡ እረፍቴ
በማያምር ፡ ቀን ፡ ወበት ፡ ድምቀቴ
የደስታዬ ፡ ድምጽ ፡ ጩኸቴ (፪x)
የለኝም ፡ ሌላ ፡ እኔ ፡ የምለዉ
ይሄ ፡ ነው ፡ ብዬ ፡ እንኳን ፡ የማነሳው ፡ ከሰው
የድስታዬ ፡ ቀኑ ፡ ባለቤት
ብቻህን ፡ ታይበት ፡ ይህን ፡ ነው ፡ የምለው
ተመሥገን ፣ ተመሥገን (፰x)
አዘኑ ፡ ክፉ ፡ ያዩልኝ ፡ ቀኖቼ
እንባን ፡ የሻቱ ፡ ለዓይኖቼ
ቀኔን ፡ አዘኸው ፡ ከላይ ፡ ከሠማይ
ጠገብኩ ፡ በደስታ ፡ ሳቅ ፡ ሲሳይ (፪x)
የለኝም ፡ ሌላ ፡ እኔ ፡ የምለዉ
ይሄ ፡ ነው ፡ ብዬ ፡ እንኳን ፡ የማነሳው ፡ ከሰው
የድስታዬ ፡ ቀኑ ፡ ባለቤት
ብቻህን ፡ ታይበት ፡ ይህን ፡ ነው ፡ የምለው
ተመሥገን ፣ ተመሥገን (፰x)
ይገባሃል ፡ ተመሥገን (፬x)
ተመሥገን (፬x)
ሀና ተክሌ 3
ዝጋብኝ
ልቤ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ይመኛል
የአንተን ፡ ጥሎ ፡ ወዲያ ፡ ይሮጣል
አሳልፈህ ፡ አትስጠኝ ፡ ለራሴ
በአንተ ፡ ልኑር ፡ አልሁን ፡ በራሴ
ልቤ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ይመኛል
የአንተን ፡ ጥሎ ፡ በራሱ ፡ ይሮጣል
አሳልፈህ ፡ አትስጠኝ ፡ ለራሴ
ደርሶ ፡ አሳቢ ፡ ስሆን ፡ ለራሴ
እንደ ፡ ልብህ ፡ ልሁን ፡ እንደልብህ
እንደ ፡ ሀሳብህ ፡ ልሁን ፡ እንደፈቃድህ (፪x)
ፈቃድህ ፡ በልቤ ፡ ላይ ፡ ትሁን
ትሰረኝ ፡ በራሴም ፡ አልሁን
ቀድመኸኝ ፡ ከወጣህ ፡ ከፊቴ
አልፈራም ፡ ብርቱ ፡ ነኝ ፡ አባቴ
ጥላህ ፡ ስር ፡ በምቾት ፡ አድራለሁ
ዘመኔን ፡ በአንተ ፡ ስር ፡ ከአደረከው (፪x)
የተከፈተ ፡ በር ፡ ሁሉ ፡ ከአንተ ፡ አይደለም
ነግ ፡ ሊያጐድለኝ ፡ እንጂ ፡ ለመልካም ፡ አይደለም
ተደባሎቆ ፡ የገባን ፡ ስኬቴን ፡ አውጣልኝ ፡ ከቤቴ ፡ ከቤቴ
ሁሉ ፡ የሞላበት ፡ የሃሰት ፡ ገነት ፡ ምን ፡ ሊበጅ ፡ ያለአንተ ፡ አንተ ፡ የለህበት
ይሻል ፡ የለ ፡ የአንተው ፡ በረሃ
ሳላይ ፡ እህል ፡ ውኃ (፪x)
ዝጋብኝ ፡ የስኬቴን ፡ መንገድ
ካልሆነ ፡ ካልመጣ ፡ ከአንተ ፡ ዘንድ
የነገን ፡ እዳ ፡ እፈራለሁ
ሰግቼ ፡ ለምን ፡ እኖራለሁ
ይቅርብኝ ፡ የምቾቴን ፡ መንገድ
ካልሆነ ፡ ካልመጣ ፡ ከአንተ ፡ ዘንድ
የነገን ፡ ቁጣ ፡ እፈራለሁ
ሰግቼ ፡ ለምን ፡ እኖራለሁ
እንደ ፡ ልብህ ፡ ልሁን ፡ እንደልብህ
እንደ ፡ ሀሳብህ ፡ ልሁን ፡ እንደፈቃድህ (፪x)
የአንተን ፡ ውድ ፡ ጊዜ ፡ መጠበቅ ፡ አቅቶኝ
የልብህን ፡ ሃሳብ ፡ መታገስ ፡ ተስኖኝ
የፈጠንኩ ፡ ሲመስለኝ ፡ ዘግይቼ
እንዳልገኝ ፡ ከአየኸው ፡ ወርጄ
የእንጀራ ፡ ጩኸቴ ፡ ፡ ጽኑ ፡ ልመናዬ
በሞላልኝ ፡ ማግስት ፡ እንዳይሆን ፡ ገዳዬ
አንተ ፡ ያልከው ፡ ይሁን ፡ በሕይወቴ
እኔ ፡ አልቅደም ፡ ቅደመኝ ፡ አባቴ
ዝጋብኝ ፡ የስኬቴን ፡ መንገድ
ካልሆነ ፡ ካልመጣ ፡ ከአንተ ፡ ዘንድ
የነገን ፡ እዳ ፡ እፈራለሁ
ሰግቼ ፡ ለምን ፡ እኖራለሁ
ይቅርብኝ ፡ የምቾቴን ፡ መንገድ
ካልሆነ ፡ ካልመጣ ፡ ከአንተ ፡ ዘንድ
የነገን ፡ ቁጣ ፡ እፈራለሁ
ሰግቼ ፡ ለምን ፡ እኖራለሁ (፪x)
እንደ ፡ ልብህ ፡ ልሁን ፡ እንደልብህ
እንደ ፡ ሀሳብህ ፡ ልሁን ፡ እንደፈቃድህ (፪x)
ሀና ተክሌ 4
የዘለዓለም ፡ ፈጣሪ
እግዚአብሔር ፡ በይሁዳ ፡ የታወቅህ
ድንኳንህ ፡ በሳሌም ፡ ማደሪያህ ፡ በጽዮን
አንተ ፡ ብርሃን ፡ ተላብሰህ ፡ ደምቀህ
ግርማዊነትህ ፡ ከዘለዓለም ፡ ተራሮች ፡ ሁሉ ፡ ይልቃል
ልበ ፡ ሙሉ ፡ የሆኑት ፡ ሁሉ ፡ አለቁ
ከተግጻጽህ ፡ የተነሳ ፡ ፈረስና ፡ ፈረሰኛው
ጭልጥ ፡ ድብን ፡ ብለው ፡ ተኙ
የያዕቆብ ፡ አምላክ ፡ ሆይ
በአንተ ፡ ፊት ፡ ማንስ ፡ መቆም ፡ ይችላል (፪x)
መፈራት ፡ ያለብህ ፡ አንተ ፡ ብቻ
መወደስ ፡ ያለብህ ፡ አንተ ፡ ብቻ
እልሃለው ፡ ዛሬም ፡ እኔም ፡ ቆሜ
አንተው ፡ በሰጠኸኝ ፡ ዘመንና ፡ ቅኔ
ልዑል ፡ ሆይ ፡ ማደሪያህ ፡ ይባረክ
ቅዱስ ፡ ሥምህ ፡ ይባረክ
ልዑል ፡ ሆይ ፡ ማደሪያህ ፡ ይባረክ (፬x)
ከኃያላኑ ፡ በፊት ፡ ኃያል
ከብርቱዎቹ ፡ በፊት ፡ ብርቱ
የነበርህ አንተ ፡ ነህ ፡ የምትኖር አንተ ፡ ነህ ፡
ፈጣሪያቸው አንተ ፡ ነህ ፡ ገዢያቸው አንተ ፡ ነህ
እግዚአብሔር አንተ ፡ ነህ ፣ አንተ ፡ ነህ
እነዚያ ፡ ዘመናቸው ፡ አልቆ ፡ ተረቱ
እንደ ፡ ቀልድ ፡ አባሩ ፡ አለፉ ፡ ተረሱ
ሲራቡ ፡ ሌላ: ነገን: ማየት
ባሉበት ፡ መዘግየት ፡ ከመሞት ፡ መሰንበት
አልቻሉም ፡ አልቻሉም
አለመሞት ፡ አልቻሉም
ነገን ፡ ማየት ፡ አልቻሉም
አልቻሉም ፡ አልቻሉም
ዝቅ ፡ ብዬ ፡ ሳይ ፡ አፈሩን
አልኩኝ ፡ አወይ ፡ አቤት ፡ አቤት
ስንት ፡ ጀግና ፡ ስንት ፡ ጐበዝ
ስንት ፡ አይደፈር ፡ ኖሯል ፡ በታች
ከምረግጠው ፡ መሬት
አሻቅቤ ፡ ሳይ ፡ ወደላይ ፡ ወደላይኛው ፡ ሠማይ
አየሁ ፡ የዘመን ፡ ልክ ፡ የዘመን ፡ ቁጥር
የዘመኑ ፡ ባለቤት ፡ የቁጥሩም ፡ ባለቤት
የሁሉን ፡ በላይ ፡ ሞትን ፡ የማያይ
መወደስ ፡ ያለበት ፡ እርሱ ፡ ብቻ
መመለክ ፡ ያለበት ፡ እርሱ ፡ ብቻ
እልሃለው ፡ እኔም ፡ ዛሬም ፡ እኔም ፡ ቆሜ
አንተው ፡ በሰጠኸኝ ፡ ዘመንና ፡ ቅኔ
ልዑል ፡ ሆይ ፡ ማደሪያህ ፡ ይባረክ
ቅዱስ ፡ ሥምህ ፡ ይባረክ
ማደሪያህ ፡ ይባረክ
ልዑል ፡ ሆይ ፡ ተባረክ
ዘለዓለምም ፡ ቢሆን ፡ የእርሱ ፡ ልክ ፡ አይደለም
መች ፡ በዚህ ፡ ይለካል ፡ የሠማይ ፡ የምድሩ ፡ የሁሉ ፡ ፈጣሪ
ኧረ ፡ እርሱ ፡ እንዲህ ፡ ነው ፡ ዘለዓለምን ፡ ፈጥሮ ፡ ወዶ ፡ በፈቃዱ
ዘለዓለምን ፡ ዘለዓለም ፡ ያኖረዋል ፡ እንጂ
ጭራሽ ፡ አይለካም ፡ እግዜሩ ፡ ክብሩ ፡ አይመዘንም
ክብሩ ፡ ለብቻው ፡ ነው ፡ ዝናው ፡ ለብቻው ፡ ነው
እስኪ ፡ አለው: ይበለኝ ፡ አንድ ፡ ሥጋ ፡ ለባሽ
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ እስኪ ፡ የትኛው ፡ ነው
የዘለዓለም ፡ ነዋሪ ፡ የዘለዓለም ፡ ፈጣሪ
የሁሉ ፡ በላይ ፡ ሞትን ፡ የማያዪ
መወደስ ፡ ያለበት ፡ እርሱ ፡ ብቻ
መከበር ፡ ያለበት ፡ እርሱ ፡ ብቻ
እልሃለው ፡ እኔም ፡ ዛሬም ፡ እኔም ፡ ቆሜ
አንተው ፡ በሰጠኸኝ ፡ ዘመንና ፡ ቅኔ
ልዑል ፡ ሆይ ፡ ማደሪያህ ፡ ይባረክ
ቅዱስ ፡ ሥምህ ፡ ይባረክ
ልዑል ፡ ሆይ ፡ ተባረክ (፪x)
ሀና ተክሌ 5
ደም ፡ ተከፍሎበታል
ለመቆሜ ፡ የምሰጠው ፡ ምክንያት ፡ አንድ ፡ ነው
አንድ ፡ አምላኬ ፡ መዳኛዬ ፡ ኢየሱስን ፡ ነው
አልተወኝም ፡ ታድጐኛል ፡ ጌታዬ (ጌታዬ)
እጄን ፡ ይዞ ፡ እንዳልወድቅ ፡ ከላላዬ
እንዳልገኝ ፡ የጠፋው ፡ ሰው ፡ ነበርኩኝ
በሃጣቴ ፡ በብዛቱ ፡ የረከስኩኝ
እኔ ፡ እንዳልገኝ ፡ የጠፋው ፡ ሰው ፡ ነበርኩኝ
ጉዳቴን ፡ እንጂ ፡ ጥቅሜን ፡ የረሳሁ ፡ በሕይወቴ (በሕይወቴ)
አዝ፦ ሕይወቴ ፡ ግን ፡ ዛሬ
ሕይወቴ ፡ ደም ፡ ተከፍሎበታል
ነፍስ ፡ ተሰጥቶበታል (፪x)
እንዳልገኝ ፡ የጠፋው ፡ ሰው ፡ ነበርኩኝ
በሃጣቴ ፡ በብዛቱ ፡ የረከስኩኝ
እኔ ፡ እንዳልገኝ ፡ የጠፋው ፡ ሰው ፡ ነበርኩኝ
በሃጣቴ ፡ በብዛቱ ፡ የረከስኩኝ
አዝ፦ ሕይወቴ ፡ ግን ፡ ዛሬ ፡ ደም ፡ ተከፍሎበታል
ሕይወቴ ፡ ነፍስ ፡ ተሰጥቶበታል
ሕይወቴ ፡ ደም ፡ ተከፍሎበታል
ሕይወቴ ፡ ሕይወቴ
ሕይወቴ ፡ ደም ፡ ተከፍሎበታል
ሕይወቴ ፡ ነፍስ ፡ ተሰጥቶበታል
ሕይወቴ ፡ ደም ፡ ተከፍሎበታል
ሕይወቴ
በቀራኒዮ ፡ ሞቱ ፡ ከሞት ፡ ድኛለሁ
በመስቀሉ ፡ ስራው ፡ ልጁ ፡ ሆኛለሁ
በክርስቶስ ፡ ደም ፡ ነጽቸአለሁ
ዕድሜዬን ፡ ዘምኔን ፡ አመልከዋለሁ
ዕድሜዬን ፡ ዘመኔን ፡ ሰትቼዋለሁ
ዕድሜዬን ፡ ዘመኔን ፡ አመልከዋለሁ
አዝ፦ ሕይወቴ ፡ ደም ፡ ተከፍሎበታል
ሕይወቴ ፡ ነፍስ ፡ ተሰጥቶበታል
ሕይወቴ ፡ ደም ፡ ተከፍሎበታል
ሕይወቴ ፡ ነፍስ ፡ ተሰጥቶበታል
ሕይወቴ
ሀና ተክሌ 6
የሮጡለትን ፡ ያዩታል
ከአንተ ፡ በፊት ፡ የቆሰሉ ፡ ብዙ ፡ አሉ ፡ ለወንጌሉ
እንደ ፡ እኔና ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ በነጻነት ፡ ዘመን ፡ ያልተፈጠሩ
ከአንቺ ፡ በፊት ፡ የተሰዉ ፡ ብዙ ፡ አሉ ፡ ለወንጌሉ
እንደ ፡ እኔና ፡ እንደ ፡ አንቺ ፡ በነጻነት ፡ ዘመን ፡ ያልተፈጠሩ
ከእኛ ፡ በፊት ፡ ብዙ ፡ አሉ ፡ የተሰዉ ፡ ለወንጌሉ
እንደ ፡ እኛ ፡ በነጻነት ፡ ዘመን ፡ ያልተፈጠሩ
ሳይሉ ፡ እጅ ፡ እግሬን ፡ ጨርቄን ፡ ማቄን ፡ በጽድቅ ፡ የኖሩ
በጌታ ፡ የተጉ ፡ ለጌታ ፡ የኖሩ ፡ በሰው ፡ የተጠሉ
አቤት ፡ የሮጡለትን ፡ ያዩታል ፡ ከወደላይ
የክብሩ ፡ ጌታ ፡ ሲያከብራቸው ፡ በሠማይ
አቤት ፡ ያዩታል ፡ ጌታን ፡ ፊት ፡ ለፊት
ሳያዩት ፡ ያመኑትን ፡ የናፈቁትን
በነፍሳቸው ፡ የጨከኑት ፡ በሥጋቸው ፡ ያከበሩት
አይገኝም ፡ አክሊላቸው ፡ በሠማይ ፡ ነው ፡ ክፍያቸው
አቤት ፡ የሮጡለትን ፡ ያዩታል ፡ ከወደላይ
ሆነው ፡ የባርነት ፡ ባሪያ ፡ ወጥተው ፡ ከሰውነት ፡ ተራ
የእኔ ፡ የሚሉት ፡ የሌላቸው ፡ ልሩጥ ፡ ለእኔም ፡ ማያቃቸው
ለወንጌል ፡ የቆሙ ፡ ለወንጌል ፡ የቀኑ
ገንዘብ ፡ የማይደፍራቸው ፡ ሰልፍ ፡ ብርታታቸው
አቤት ፡ የሮጡለትን ፡ ያዩታል ፡ ከወደላይ
የክብሩ ፡ ጌታ ፡ ሲያከብራቸው ፡ በሠማይ
አቤት ፡ ያዩታል ፡ ጌታን ፡ ፊት ፡ ለፊት
ሳያዩት ፡ ያመኑትን ፡ የናፈቁት
በነፍሳቸው ፡ የጨከኑት ፡ በሥጋቸው ፡ ያከበሩት
አይገኝም ፡ አክሊላቸው ፡ በሠማይ ፡ ነው ፡ ክፍያቸው
አቤት ፡ ያዩታል ፡ ጌታን ፡ ፊት ፡ ለፊት
ማነው ፡ ታዲያ ፡ የዘምኔ ፡ አርበኛ
ለጌታ ፡ ነገር ፡ ያልተኛ
ብድራቱንስ ፡ ያልተቀበለ
እውነት ፡ ለወንጌል ፡ የጨከነ
በነጻነት ፡ ዘመን ፡ ራሱን ፡ የሰዋ
ለጥቅም ፡ ያልኖረ ፡ በእምነቱ ፡ የጸና
ማነው ፡ የዘምኔ ፡ ወንጌል ፡ ነጋሪ
በተግባር ፡ የታየ ፡ የጽድቅ ፡ ተባባሪ
ያልሆነ ፡ በፍፁም ፡ የነጻነት ፡ ባሪያ
ከቶ ፡ ያልተገኘ ፡ እዚህ ፡ ሲሉት ፡ እዚያ
ማነው ፡ የአቋም ፡ ሰው ፡ ዘመን ፡ ተሻጋሪ
ሰልፍ ፡ እየበረታ ፡ ወንጌሉን ፡ ዘማሪ
ማነው ፡ የዘመኔ ፡ ባለ ፡ አክሊል ፡ ተረኛ
ለራሱ ፡ ያልኖረ ፡ ከሥጋው ፡ ጠበኛ
ሞትን ፡ ጥቅሜ ፡ ብሎ ፡ በነፍሱ ፡ የጨከነ
ግራ ፡ ቀኝ ፡ ያላየ ፡ ለቃሉ ፡ የታመነ
ማነው ፡ የዘምኔ ፡ አርበኛ ፡ ማነው
አቤት ፡ የሮጡለትም ፡ ያዩታል ፡ ከወደላይ
የክብሩ ፡ ጌታ ፡ ሲያከብራቸው ፡ በሠማይ
ሀና ተክሌ 7
ያዛኝ ፡ ያለህ
ማን ፡ ያመልጣል ፡ ከእግዚአብሔር
ማን ፡ ይሸሸጋል ፡ ከጌታ
ቢገለጥ ፡ ታሪካችን
ጉድ ፡ ነው ፡ የእኛ ፡ ገበና
በአደባባይ ፡ ጨዋ ፡ ያረገን
በግል ፡ መክሮ ፡ ያሳፈረን
ዳኝነቱ ፡ ያልተገባን
እኔን ፡ ጨምሮ ፡ ቤቱ ፡ ይቁጠረን
ነግ ፡ በእኔ ፡ ማለት ፡ ጥሩ
በተያዙበት ፡ መያዝ ፡ ሳይያዙ
ጌታን ፡ እንደው ፡ እርሱ ፡ ይምራል
ይህንንም ፡ ይቅር ፡ ይላል (፪x)
ምህረት ፡ የናቀ ፡ ዛሬም ፡ ይፈርዳል
በተማረው ፡ ልክ ፡ ማን ፡ ሰው ፡ ይምራል (፪x)
እንከን ፡ የለሽ ፡ ኑሮ ፡ የለኝም
ታሪኬ ፡ ቢመረመር
ሌላው ፡ ላይ ፡ ስፍረድ ፡ ቆሜ
ወድቆ ፡ እስኪሰበር
የእርሱን ፡ ገሃድ ፡ የእኔ ፡ በቤቴ
ፍርድ ፡ ገምድሎ ፡ የማንነቴ
ብዙ ፡ የተማረ ፡ ብዙ ፡ ይምራል
ነበር ፡ ትምህርቱ ፡ ማን ፡ ግድ ፡ ይለዋል?
አምላክ ፡ አድርጐለት ፡ ሃጥያቱን ፡ ታሪክ
ሰው ፡ አልምር ፡ ብሎት ፡ ሆነ ፡ የዕድሜ ፡ ልክ
አትፍረጅ ፡ አትፍረጅ ፡ ተይ ፡ ነፍሴ
ይፈረድብሻል ፡ አንቺ ፡ ተይ ፡ ምላሴ
እያየሽ ፡ እየኖርሽ ፡ የእርሱን ፡ ምህረት
እንዴት ፡ ግድ ፡ አይልሸም ፡ የሰው ፡ ሕይወት
የማያልፈው ፡ . (1) . ፡ የእራሱን ፡ ቁስለት
አያቆም ፡ መፍረድ ፡ በሰውም ፡ ማንነት
ለከፋ ፡ ቁስል ፡ እንጨት ፡ ይሰዳል
ለታመመ ፡ ሰው ፡ ይህ ፡ መች ፡ ይረዳል
ኧረ ፡ ያዛኝ ፡ ያለህ ፡ ይላል ፡ ጪኸቱ
አላሳልፍ ፡ ቢለው ፡ የሰው ፡ አንደበቱ
በሰው ፡ አፍ ፡ ተመቶ ፡ እያነከሰ
ስንቱ ፡ ተሰብሮ ፡ ከማይሆን ፡ ዋለ ፡ አሃሃ
ማን ፡ ያመልጣል ፡ ከእግዚአብሔር
ማን ፡ ይሸሸጋል ፡ ከጌታ
ቢገለጥ ፡ ታሪካችን
ጉድ ፡ ነው ፡ የእኛ ፡ ገበና
በአደባባይ ፡ ጨዋ ፡ ያረገን
በግል ፡ መክሮ ፡ ያሳፈረን
ዳኝነቱ ፡ ያልተገባን
እኔን ፡ ጨምሮ ፡ ቤቱ ፡ ይቁጠረን
ነግ ፡ በእኔ ፡ ማለት ፡ ጥሩ
በተያዙበት ፡ መያዝ ፡ ሳይያዙ
ጌታን ፡ እንደው ፡ እርሱ ፡ ይምራል
ይህንንም ፡ ይቅር ፡ ይላል (፪x)
ምህረት ፡ የናቀ ፡ ዛሬም ፡ ይፈርዳል
በተማረው ፡ ልክ ፡ ማን ፡ ሰው ፡ ይምራል (፪x)
ሀና ተክሌ 8
ሰላም ፡ ነው
መኖሪያዬ ፡ የዘላለም ፡ አምላክ
የአባቶቼ ፡ የነ ፡ ሙሴ ፡ ኣባት
እንደ ፡ እግዚኣብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም
የሚያውቅልኝ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ አላገኝም
ብታድነኝም ፡ ባታዳነኝም ፡ አንተ ፡ መልካም ፡ ነህ
ይህንን ፡ አድርግ ፡ ያንን ፡ አታድርግ ፡ መች ፡ ትባላለህ
ላደረራግህ ፡ ማስተካከያ ፡ ከማንም ፡ ኣትሻም
ፍፁም ፡ በስራህ ፡ ፍፁም ፡ በምክርህ ፡ አትሳሳትም
ያስጨነቀኝ ፡ ቀንበሬን ፡ ውስጤን ፡ አንቆ ፡ የያዘው
ለእኔ ፡ እንጂ ፡ ቢከብደኝ ፡ ኢየሱሴ ፡ ለአንተ ፡ እንዴት ፡ እንዴት ፡ ቀላል ፡ ነው
የዛሬው ፡ ድቅድቅ ፡ ሌሊቴ ፡ ይገባሃል ፡ ሚስጥሩ
ፊትህን ፡ አያየሁ ፡ ዛሬ ፡ ግን ፡ አላለሁ ፡ ሰላም ፡ ነው
አዝ፦ ሰላም ፡ ነው ፡ እላለሁ ፡ በእጅህ ፡ የገባውን ፡ ነገሬን ፡ እያየሁ
ሰላም ፡ ነው ፡ እላለሁ ፡ ውስጤ ፡ ሸክም ፡ አዝሎ ፡ እጅህን ፡ አያየሁ
አልገባሽ ፡ ቢለኝ ፡ ነገሩ ፡ ማዕበሉን ፡ ወጀቡን ፡ ፈርቼ
ውስጤ ፡ ብርዱ ፡ ተሰማኝ ፡ ሰው ፡ ነኝና ፡ ሰግቼ
ጉልበቴ ፡ እልሃለሁ ፡ ዛሬ ፡ አቅሜ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ አቤቱ
እምነቴ ፡ እንደው ፡ አልታመነም
አይተኸኛል ፡ በብዙ ፡ ግን ፡ እላለሁ
አዝ፦ ሰላም ፡ ነው ፡ እላለሁ ፡ ያደረክልኝ ፡ ትናንትን ፡ እያየሁ
ሰላም ፡ ነው ፡ እላለሁ ፡ በዚህ ፡ ኣይቀጥልም ፡ ክብርህን ፡ አያለሁ
ሰላም ፡ ነው ፡ እላለሁ ፡ ያደረክልኝ ፡ ትናንትን ፡ እያየሁ
ሰላም ፡ ነው ፡ እላለሁ ፡ ይህም ፡ ሌሊት ፡ ያልፋል ፡ ክብርህን ፡ አያለሁ
ደህና ፡ ነው ፡ ካለች ፡ ሱንማይቷ
የአንድ ፡ ልጇን ፡ ነፍስ ፡ ኣጥታ ፡ ከቤቷ
ታድያ ፡ እንዴት ፡ አልል ፡ ሰላም ፡ ነው
ባለቤት ፡ አለኝ ፡ የኔ ፡ አይደለሁም
በትንሽ ፡ ትልቁ ፡ ብዙ ፡ ጭንቀቴ
መልስ ፡ እንዳይሆነኝ ፡ ለዘመመው ፡ ቤቴ
ተረድቻለሁ ፡ ይህንን ፡ አውቄአለሁ
ነገሬን ፡ ሁሉ ፡ አስረክቤዋለሁ
መኖሪያዬ ፡ የዘላለም ፡ አምላክ
ያባቶቼ ፡ የነ ፡ ሙሴ ፡ ኣባት
እንደ ፡ እግዚኣብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም
የሚያውቅልኝ ፡ አንደአንተ ፡ አላገኝም
ብታድነኝም ፡ ባታዳነኝም ፡ አንተ ፡ መልካም ፡ ነህ
ይህንን ፡ አድርግ ፡ ያንን ፡ አታድርግ ፡ መች ፡ ትባላለህ
ላደረራግህ ፡ ማስተካከያ ፡ ከማንም ፡ ኣትሻም
ፍፁም ፡ በሥራህ ፡ ፍፁም ፡ በምክርህ ፡ አትሳሳትም
ሰላም ፡ ነው (፬x)
ሰላም ፡ ነው (፬x)
አውጃለሁ ፡ ዛሬም ፡ መልካምንትህን ፡ ባልሞላው ፡ ነገሬ
ስንፍና ፡ አልሰብክም ፡ ዕምነቴን ፡ አልጥልም ፡ ከንቱ ፡ ተናገሬ
ከአንተ ፡ በላይ ፡ ለእኔ ፡ ለመጪው ፡ ዘመኔ ፡ እኔ ፡ አላውቅምና
መቆዘሜን ፡ ጥዬ ፡ ይህም ፡ ያልፋል ፡ ብዬ ፡ ልለፍ ፡ በምሥጋና
ብርቱ ፡ ሰልፍ ፡ ሲሆን ፡ ሕይወቴ
እንድማር ፡ ነው ፡ አባቴ
ነፋሱ ፡ ሲያይል ፡ ሲበረታ
ድንቅህን ፡ ላይ ፡ ነው ፡ የማታ ፡ የማታ (፪x)
ብርቱ ፡ ሰልፍ ፡ ሲሆን ፡ ህይወቴ
ለትምህርቴ ፡ ነው ፡ አባቴ
ወጀቡ ፡ ቢያይል ፡ ቢበረታ
ግን ፡ ድሉ ፡ የእኔ ፡ ነው ፡ የማታ ፡ የማታ (፪x)
ሰላም ፡ ነው (፬x)
ሰላም ፡ ነው (፬x)
ሀና ተክሌ 9
ወቅት ፡ እንዳታበላሽ
ክረምት ፡ አልጠብቅም ፡ ክረምት ፡ ላይ ፡ ሆኜ
በጋን ፡ እኔ ፡ አልሻም ፡ በጋ ፡ ላይ ፡ ቁጭ ፡ ብዬ
እሰራለሁ ፡ አሁን ፡ ስራዬን ፡ አለቅም
ዘመኔ ፡ ላይ ፡ ቆሜ ፡ ዘመን ፡ አልጠብቅም
ጊዜዬ ፡ ነው ፡ ወቅቴ ፡ ነው ፡ ዘመኑ ፡ ነው ፡ ተራዬ
እሰራለሁ ፡ እሮጣለሁ ፡ በወቅቱ ፡ ዘርቼ ፡ ከእርሱ ፡ እጠብቃለሁ
ይረዳኛል ፡ አምናለሁ ፡ የተሰጠኝ ፡ ጊዜዬ ፡ ነው
እሰራለሁ ፡ እሮጣለሁ ፡ በወቅቱ ፡ ዘርቼ ፡ ከእርሱ ፡ እጠብቃለሁ
በጊዜ (፬x)
ትናንት ፡ ላልሆነለት ፡ ዛሬን ፡ አትንፈገው
ከንፈርህን ፡ መጠህ ፡ ሁድህን ፡ አታስብሰው
ተስፋ ፡ ለቆረጠው ፡ ምክር ፡ ካስፈለገ
ዐይኑን ፡ ግለጥና ፡ አድርሰው ፡ ለነገ
ትናንት ፡ ዛሬ ፡ አይደለም ፡ ዛሬ ፡ ሌላ ፡ ቀን ፡ ነው
በትላንቱ ፡ ዛሬ ፡ ዛሬን ፡ ያረሰ ፡ ማነው
የመጠውለግ ፡ ጸባይ ፡ አይሆንም ፡ ወዳጄ
ወቅት ፡ እንዳታበላሽ ፡ ልንገርህ ፡ ማልጄ
በጊዜ (፬x)
አሁን ፡ የዋልንበት ፡ ነው ፡ ለነገ ፡ ተስፋ
የዘራነው ፡ ዘር ፡ ነው ፡ ሚጠብቀን ፡ ኋላ
ከሰራነው ፡ ዛሬን ፡ ከተጋን ፡ በበርቱ
እንደርሳለን ፡ ካልነው ፡ አይቀርም ፡ መድረሱ
በጊዜ (፬x)
ክረምት ፡ አልጠብቅም ፡ ክረምት ፡ ላይ ፡ ሆኜ
በጋን ፡ እኔ ፡ አልሻም ፡ በጋ ፡ ላይ ፡ ቁጭ ፡ ብዬ
እሰራለሁ ፡ አሁን ፡ ስራዬን ፡ አለቅም
ዘመኔ ፡ ላይ ፡ ቆሜ ፡ ዘመን ፡ አልጠብቅም
ጊዜዬ ፡ ነው ፡ ወቅቴ ፡ ነው ፡ ዘመኑ ፡ ነው ፡ ተራዬ
እሰራለሁ ፡ እሮጣለሁ ፡ በወቅቱ ፡ ዘርቼ ፡ ከእርሱ ፡ እጠብቃለሁ
ይረዳኛል ፡ አምናለሁ ፡ የተሰጠኝ ፡ ጊዜዬ ፡ ነው
እሰራለሁ ፡ እሮጣለሁ ፡ በወቅቱ ፡ ዘርቼ ፡ ከእርሱ ፡ እጠብቃለሁ
በጊዜ (፬x)
ሀና ተክሌ 10
በጉባኤው ፡ መሃል
በጉባኤው ፡ መሃል ፡ በአንድ ፡ አባት ፡ ልጆች ፡ ላይ
የተገፋፋ ፡ ሰው ፡ አንድ ፡ ላይ ፡ ያመልክሃል
አንድ ፡ ላይ ፡ ያመልካል
ውስጡን ፡ እያመመው ፡ ጥላቻው ፡ በርትቶ
ወድሃለው ፡ ይላል ፡ ህዝብህ ፡ ቤትህ ፡ ገብቶ
አንድ ፡ ላይ ፡ ተቀምጦ
ስንበላም ፡ አንድ ፡ ላይ
ስንጠጣም ፡ አንድ ፡ ላይ
ስንገባም ፡ አንድ ፡ ላይ
ስንወጣም ፡ አንድ ፡ ላይ
ይህን ፡ ሁሉ ፡ ዘምን ፡ አንድ ፡ ላይ ፡ ኖረናል
ውስጥ ፡ ውስጡን ፡ ተባልተን ፡ ግን ፡ ተለያይተናል
ምን ፡ ያደርጋል
ፍቅር ፡ አይደለም ፡ ዎይ ፡ ያገናኘን
ፍቅር ፡ አይደለም ፡ ዎይ ፡ ያሰባሰበን
ኢየሱስ ፡ አይደለም ፡ ዎይ ፡ ያገናኘን
ጌታ ፡ አይደለም ፡ ዎይ ፡ ያሰባሰበን
የስስት ፡ ጨርቃችን ፡ መጨረሻው ፡ ብል፡ ነው
ለዛሬ ፡ ያልሆነ ፡ ፍቅራችን ፡ ለመች ፡ ነው
ኧረ ፡ ለማንስ ፡ ነው
ከፍቅሩ ፡ ባለቤት ፡ ከሆነ ፡ ውሎዋችን
በአንድነት ፡ ይገለጥ ፡ እውነት ፡ አምልኳችን
በፍቅር ፡ አምልኳችን
ስንበላም ፡ አንድ ፡ ላይ
ስንጠጣም ፡ አንድ ፡ ላይ
ስንገባም ፡ አንድ ፡ ላይ
ስንወጣም ፡ አንድ ፡ ላይ
ይህን ፡ ሁሉ ፡ ዘምን ፡ አንድ ፡ ላይ ፡ ኖረናል
ውስጥ ፡ ውስጡን ፡ ተባልተን ፡ ተለያይተናል
ምን ፡ ያደርጋል
ፍቅር ፡ አይደለም ፡ ዎይ ፡ ያገናኘን
ፍቅር ፡ አይደለም ፡ ዎይ ፡ ያሰባሰበን
ኢየሱስ ፡ አይደለም ፡ ዎይ ፡ ያገናኘን
ጌታ ፡ አይደለም ፡ ዎይ ፡ ያሰባሰበን
እምነት ፡ ቢሞላ ፡ ዕውቀት ፡ ቢከበኝ
ልሳን ፡ መናገር ፡ ትንቢት ፡ ቢኖረኝ
ሥጋዬን ፡ ለእሳት ፡ ብሰጥ ፡ ፈቅጄ
ባልነፍግ፡ ለድሆች ፡ ያለኝን ፡ ከእጄ [1]
ፍቅር ፡ የሌለው ፡ እልፍ ፡ ደግነት
ጌታ ፡ የሌለበት ፡ መንፈሳዊነት
ወዴት ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ ይህ ፡ ከንቱ ፡ ጉዞ
በሃሜት ፡ ታዝሎ ፡ በቂም ፡ ተይዞ
ዞሮ ፡ ለማን ፡ ነው ፡ ይህ ፡ ጥል ፡ ግርግር
አቤል ፡ ከቃየል ፡ የማይሆን ፡ አጥር
ጐራ ፡ ለይቶ ፡ ይቅር ፡ ማድሩ
የእውነት ፡ ፍቅር ፡ ይግባ ፡ መንደሩ
የባላንጣችን ፡ ደስታው ፡ ይደፍርስ
በፍቅር ፡ ዘምተን ፡ ሰላም ፡ እንመልስ
የቁርሾን ፡ ዘመን ፡ ይበቃ ፡ ብለነው
መዘናጠሉ ፡ ነው ፡ ወዲያ ፡ እንጣለው
ፍቅር ፡ ይበቀለው
በረከት ፡ ደርሶ ፡ ደጅ ፡ አይመለስ
የተወሰድው ፡ ክብርም ፡ ይመለስ
ፍቱን ፡ መድሃኒት ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ፈውሱ
ለምድሪቱ ፡ ቀውስ ፡ ጥያቄ ፡ መልሱ
ፍቅር ፡ አይደለም ፡ ዎይ ፡ ያገናኘን (፪x)
ኢየሱስ ፡ አይደለም ፡ ዎይ ፡ ያገናኘን
ጌታ ፡ አይደለም ፡ ዎይ ፡ ያሰባሰበን
ሀና ተክሌ 11
ያለ ፡ ምክንያት
ስፈራ ፡ ስቸር ፡ ማልተነፍሰው ፡ ሚስጥሬ ፡ በዝቷል
እኔ ፡ ባልናገር ፡ የልብ ፡ ወዳጄ ፡ የውስጤን ፡ ያውቃል
እርሱ ፡ እንደሚያውቀኝ ፡ ሰው ፡ አያውቀኝም ፡ እንጂ
መቆም ፡ አልችልም ፡ እንኳን ፡ በንጉሥ ፡ በራሴም ፡ ደጅ
የምህረት ፡ ዓይኑ ፡ ዛሬም ፡ ያየኛል
አልሰለቸኝም ፡ ይፈልገኛል (፪x)
ፈላጊዬ ፡ መሃሪዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ወዳጄ
አይዞሽ ፡ የሚለኝ ፡ እኔን ፡ ሚያበረታኝ
ነው ፡ የልብ ፡ ወዳጄ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ
እንዳትወደኝ ፡ በመልካምነቴ
ይህ ፡ አይደለም ፡ ማንነቴ
እንዳትጠላኝ ፡ ደግሞ ፡ በጥፋቴ
ፍቅር ፡ ነህ ፡ አያስችልህም ፡ አባቴ
ያለ ፡ ምክንያት ፡ ወደህ ፡ በምክንያት ፡ አትጠላም
ለምህረትህ ፡ ስፍር ፡ መለኪያ ፡ የለውም
የአንተ ፡ ፍቅር ፡ መነሺያው ፡ ከራስህ
የመውደድ ፡ ልብ ፡ የማያልቅብህ (፪x)
የእኔ ፡ ጌታ
ከወዳጅ ፡ ከፍቶ ፡ ልጅህ ፡ ድርሻዬን ፡ ብሎ ፡ እርም ፡ እንዳላለ
አልመች ፡ ቢለው ፡ የሸፈተበት ፡ አባቴን ፡ አለ
አባትነቱን ፡ የበደል ፡ ብዛት ፡ መች ፡ ይሽረዋል
ሁልን ፡ እረስቶ ፡ ደግሞ ፡ እንደገና ፡ ልጄ ፡ ይለዋል
በምህረት ፡ ዓይኑ ፡ ዛሬም ፡ ያየኛል
አልሰለቸኝም ፡ ይፈልገኛል
የምህረት ፡ ዓይኑ ፡ ዛሬም ፡ ያየኛል
አልሰለቸኝም ፡ ይፈልገኛል
ፈላጊዬ ፡ መሃሪዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ወዳጄ
አይዞሽ ፡ የሚለኝ ፡ እኔን ፡ ሚያበረታኝ
ነው ፡ የልብ ፡ ወአጄ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ
ሀና ተክሌ 12
ድሮዬን ፡ አልደግምም
አላስተያይህም ፡ ከሚሆነው ፡ ከሁኔታው ፡ ጋራ
ከሚመጣው ፡ ዳግም ፡ ከሚሄደው ፡ ከንፋስ ፡ ሽውታ
ምክንያቱ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ አንተን ፡ የማመልክበት
በቂ ፡ ነው ፡ መዳኔ ፡ ከበቂም ፡ በላይ ፡ ነው ፡ መትረፌ
ኢህን ፡ በሥልጣኑ ፡ ማድረግ ፡ ማን ፡ ቻለበት
አይደለም ፡ ዎይ ፡ ያወጣኸኝ ፡ ከባርነት
አይደለም ፡ ዎይ ፡ የፈታኸኝ ፡ ከእስራት
ታዲያ ፡ እንዴት ፡ ነው ፡ መኖሩ
ዳግም ፡ ተለይቶ ፡ ወጥቶ ፡ ከነጻነት
ድሮዬን ፡ አልሻም ፡ ድሮዬን ፡ አልደግምም
እኔ ፡ አልመለስም ፡ እስር ፡ ቤት
አዝ፦ እኔ ፡ አልመለስም ፡ እስር ፡ ቤት
አልመለስም ፡ እስር ፡ ቤት (፫x)
ውሻ ፡ ወደ ፡ ትፋቱ ፡ እንዲመልስ
አልገኝም ፡ ኋላዬን ፡ ስከልስ
የያዝኩት ፡ መንገድ ፡ ገብቶኛል
ልክ ፡ ነው ፡ ማን ፡ ያስተኛል
ሕይወት ፡ ነው ፡ እውነት ፡ የሞላበት
የሰላም ፡ ነው ፡ ቤቱ ፡ ያለንበት
እጠራለሁ ፡ እንጂ ፡ ሌላውን
ያልገባውን ፡ ያላየዉን
እኔ ፡ አልመለስም ፡ እስር ፡ ቤት
አዝ፦ አልመለስም ፡ እስር ፡ ቤት (፪x)
እኔ ፡ አልመለስም ፡ እስር ፡ ቤት (፪x)
አልመለስም ፡ እስር ፡ ቤት (፪x)
እኔ ፡ አልመለስም ፡ እስር ፡ ቤት (፪x)
ዴማስን : ሳልሆን ፡ ተላላ
መንገድ ፡ ላይ ፡ ሳልቀር ፡ ከኋላ
ከመቅበዝበዝ ፡ ሕይወት ፡ ድኛለሁ
ከዓለም ፡ ፍቅር ፡ ተርፊያለሁ
ዘምራለው ፡ ከቶ ፡ አልዘፍንም : ቆሜ
ጾሜ ፡ ታች ፡ አልወርድም እላይ ፡ ተሰይሜ
አበራለሁ ፡ ገና ፡ መዳኔን
ብርቁን ፡ ታሪክ ፡ የኢየሱሴን
እኔ ፡ አልመለስም ፡ እስር ፡ ቤት
አዝ፦ አልመለስም ፡ እስር ፡ ቤት (፪x)
እኔ ፡ አልመለስም ፡ እስር ፡ ቤት (፪x)
እኔ ፡ አልመለስም ፡ እስር ፡ ቤት (፪x)
አልመለስም ፡ እስር ፡ ቤት (፪x)
ሀና ተክሌ 13
ፍሰሃዬ
የምፈልገውን ፡ ሁሉ ፡ ባገኝ
የምፈልገው ፡ ደስታ ፡ ጋራ ፡ አልደርስም
ስደርስበት ፡ ይቀልብኛል
ሳልጠግበው ፡ ይሰለቸኛል
የእኔ ፡ ክፍተት ፡ ሌላ ፡ ነው
ብርም ፡ ወርቅም ፡ አይደለም
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ረሃቤ
መንፈስ ፡ ነው ፡ ጥጋቤ
በህልውናህ ፡ ሥር ፡ መሆን
በአንተ ፡ መኖር ፡ ውሎ ፡ ማደር
በመገኘትህ ፡ የታሰበ ፡ ሰዉ
ምነኛ ፡ የታደለ ፡ ነው
አስበኝ ፡ የእኔንም ፡ በህልውናህ
በሚያጽናናው ፡ በመንፈስህ
ይህ ፡ ነው ፡ ጥማቴ ፡ ይህ ፡ ነው ፡ ጉጉቴ
ክብርህን ፡ ማየት ፡ ነው ፡ መሻቴ
ትርጉም ፡ ለጠፋው ፡ ሕይወቴ
ምላሽ ፡ ሲታጣ ፡ ከሞላው ፡ ቤቴ
ለሞኖር ፡ ስዝል ፡ ሲደክመኝ
ባዶነቴ ፡ ሲጮህብኝ
የእኔ ፡ ክፍተት ፡ ሌላ ፡ ነው
ያለኝ ፡ ነገር ፡ አይደለም
ኢየሱስ ፡ ነህ ፡ ረሃቤ
መንፈስው ፡ ነው ፡ ጥጋቤ
በህልውናህ ፡ ሥር ፡ መሆን
በአንተ ፡ መኖር ፡ ውሎ ፡ ማደር
በመገኘትህ ፡ የታሰበ ፡ ሰዉ
ምነኛ ፡ የታደለ ፡ ነው
አስበኝ ፡ የእኔንም ፡ በህልውናህ
በሚያጽናናው ፡ በመንፈስህ
ይህ ፡ ነው ፡ ጥማቴ ፡ ይህ ፡ ነው ፡ ጉጉቴ
ክብርህን ፡ ማየት ፡ ነው ፡ መሻቴ
ህልሜ ፡ አንተን ፡ ማየት ፡ በኑሮዬ
ህልሜ ፡ አንተን ፡ ማየት ፡ ነው ፡ ጉጉቴ
የደስታዬ ፡ ልክ ፡ ሰላሜ ፡ እርካታዬ
ጥግ ፡ ፍስሃዬ ፡ ኢየሱስ
ይህ ፡ ነው ፡ ጥማቴ ፡ ይህ ፡ ነው ፡ ጉጉቴ
ክብርህን ፡ ማየት ፡ ነው ፡ መሻቴ (፪x)
ሀና ተክሌ 14
በፀሎት
ሰውማ ፡ የእራሱ ፡ ችግር ፡ በዝቶበት፥
ያዋየዋል ፡ ለጠናበት፤
ለእራሱ ፡ መሆን ፡ አቅቶት፥
ጭንቀት ፡ ሰፎት፤
ማን ፡ ሊረዳው ፡ ማን ፡ አቤት ፡ ብሎት
ውይ ፡ ሰው ፡ አልኩኝ ፡ እኔም ፡ በችግሬ
ሁሉም ፡ ሲሰወር ፡ ከሰፈሬ
አለሁ ፡ ያለኝ ፡ በደህና : ቀን
ውሉ ፡ ጠፋብኝ ፡ በከፋኝ ፡ ቀን
ዘወር ፡ ስል ፡ ከሰውም ፡ ከእራሴ
ጌታ ፡ ነው ፡ ለካ ፡ መልሴ
በይ ፡ ፀሎቴ (፪x)
ዛሬ ፡ አገናኚኝ ፡ ቶሎ ፡ ከአባቴ
ባለቅስ ፡ ተደፍቼ ፡ እግሩ ፡ ሥር ፡ ወድቄ
ስነሳ ፡ ፊቴ ፡ በርቶ ፡ ልቤ ፡ በእርሱ ፡ ረክቶ
ቢመለስም ፡ ባይመለስም ፡ ጥያቄው
ውስጤ ፡ ሰላም ፡ ነው
ከእኔ ፡ በላይ ፡ የሚያስብልኝ ፡ እርሱ ፡ አዋቂ ፡ ነው
ብቻ ፡ አልሰወር ፡ አልጥፋ ፡ እንጂ ፡ እኔ ፡ ከሥሩ
እንኳን ፡ ነገሬን ፡ እኔ ፡ አልፈዋለሁ ፡ ሙሉ ፡ ዘመኑን
(በፀሎት)
መልስ ፡ ይመለሳል ፡ በፀሎት
ልብ ፡ ይጠበቃል ፡ በፀሎት
በፀሎት ፡ በመንበርከክ (፪x)
ቅርብ ፡ ነው ፡ አጠገቤ ፡ ነው ፡ ጌታዬ
የእኔ ፡ የሚለኝ ፡ ወዳጄ
ታዲያ ፡ 'ለማን?' ፡ 'ለምን?' ፡ ብዬ ፡ እጨነቃለሁ
ልመናዬን ፡ አስታውቃለሁ
አእምሮን ፡ የሚያልፍ ፡ የአምላክ ፡ ሰላም
ልቤን ፡ ሃሳቤን ፡ ይጠብቃል
ደስ ፡ ይለኛል ፡ በእርሱ ፡ ሁልጊዜ
ላይቀር ፡ ያለልኝ ፡ ባለው ፡ ጊዜ
ሲገባኝ ፡ እውነቱ ፡ ለእራሴ
ጌታ ፡ ነው ፡ ለካ ፡ መልሴ
በይ ፡ ፀሎቴ (፪x)
ዛሬ ፡ አገናኚኝ ፡ ቶሎ ፡ ከአባቴ
ባለቅስ ፡ ተደፍቼ ፡ እግሩ ፡ ሥር ፡ ወድቄ
ስነሳ ፡ ፊቴ ፡ በርቶ ፡ ልቤ ፡ በእርሱ ፡ ረክቶ
ቢመለስም ፡ ባይመለስም ፡ ጥያቄው
ውስጤ ፡ ሰላም ፡ ነው
ከእኔ ፡ በላይ ፡ የሚያስብልኝ ፡ እርሱ ፡ አዋቂ ፡ ነው
ብቻ ፡ አልሰወር ፡ አልጥፋ ፡ እንጂ ፡ እኔ ፡ ከሥሩ
እንኳን ፡ ነገሬን ፡ እኔ ፡ አልፈዋለሁ ፡ ሙሉ ፡ ዘመኑን
(በፀሎት)
መልስ ፡ ይመለሳል ፡ በፀሎት
ልብ ፡ ይጠበቃል ፡ በፀሎት
በፀሎት ፡ በመንበርከክ (፪x)
በፀሎት ፡ በፀሎት ፡ በፀሎት (፪x)
ሀና ተክሌ 15
ቤተ ፡ ሰሪ
ባማረ ፡ ባጌጠ ፡ ቤት ፡ ውስጥ ፡ ተሰይሚያለሁ
በተዋበ ፡ ህዝብ ፡ ተከብቢያለሁ
ዙሪያዬን ፡ የማየው ፡ ሁሉ ፡ ለዓይን ፡ ይስባል
እኔ ፡ ግን ፡ ታምሜ ፡ ውበቴ ፡ ጠፍቶኛል
ከቤትህ ፡ ውስጥ ፡ እያለሁ ፡ እኔ ፡ ጐድያለሁ
ለሚያየኝ ፡ ለስሞት ፡ እኔ ፡ እንዳለሁ ፡ አለሁ
ቤትህን ፡ ሲሞላው ፡ ዕልልታና ፡ ሆታ
እኔን ፡ የሚያውከኝ ፡ የነፍሴ ፡ ጭንቀቷ
የአንተ ፡ ቤት ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ የእኔ ፡ ቤት ፡ ሌላ ፡ ነው
ቤተ ፡ ሰሪው ፡ በዝቶ ፡ መላ ፡ የሚለኝ ፡ ማነው
ቀርበህ ፡ ሳለህ ፡ ከደጅ ፡ ልትመጣ ፡ ወዳጄ
እንዴት ፡ ይሆን ፡ የማይህ ፡ እሩቅ ፡ አገር ፡ ሄጄ
ያዳራሹ ፡ ውበት ፡ እኔን ፡ ሸፍኖኛል
ግዑዝ ፡ ከእኔ ፡ በልጦ ፡ አልፎ ፡ ይኮንነኛል
በጌጥ ፡ የታጀበ ፡ ቤቱ ፡ ተሰርቶ ፡ አልቆ
ልብ ፡ ሁሉ ፡ በእጁ ፡ ነው ፡ የእኔን ፡ ቦታ ፡ ወስዶ
ይበል ፡ እርሱም ፡ ይመር ፡ ቦታም ፡ አይጥበበን
ግን ፡ ለታደሰ ፡ ቤት ፡ ምነው ፡ አጉል ፡ አጉል ፡ ሆነ
እኔ ፡ ካልተደስኩኝ ፡ ካልሆንኩኝ ፡ እንደ ፡ ቤቱ
ትርጉም ፡ የለሽ ፡ ኑሮ ፡ ድካም ፡ ነው ፡ ለከንቱ
ቀኑ ፡ ቀርቧል ፡ እያልን ፡ ፍጻሜ ፡ የዘመን
ከንቱ ፡ ቤት ፡ ስንሰራ ፡ ዘለዓለሙን ፡ ትተን
ተላልፈን ፡ እንዳንቀር ፡ አቤቱ ፡ አደራ
የተጣልን ፡ እንዳንሆን ፡ እንደነበርን ፡ ሥምህን ፡ ስንጠራ
ሥምህን ፡ ስንተጠራ ፡ ሥምህን
አደራ ፡ የነበርን
ሥምህን ፡ ስንጠራ